Logo
EBC
አስቶን ቪላ የዩሮፓ ሊግ ዋንጫን አሸነፈ
************
በዩሮፓ ሊግ ውድድር የፍፃሜ ጨዋታ የዩናይ ኢምሬው አስቶን ቪላ የጀርመኑን ፍሬይቡርግን 3 ለ 0 አሸንፏል።

በቱርክዬ ኢስታንቡክ ከተማ በተደረገውን ጨዋታ ለአስቶን ቪላ የማሸነፊያ ግቦቹን ዩሪ ቴሊስማን፣ ቡዬንዳ እና ሞርጋን ሮጀርስ አስቆጥረዋል።

በዩሮፓ ሊግ የተለያዩ ክለቦችን እያሰለጠኑ ለስድስተኛ ጊዜ ለዋንጫ የደረሱት ዩናይ ኢምሬ፤ ከዚህ ቀደም ከሴቪላ እና ቪያሪያል ጋር አራት የዩሮፓ ሊግ ዋንጫዎችን ማንሳታቸው ይታወሳል።

ዩናይ ኢምሬ የዛሬውን ጨምሮ በውድድሩ 5 ዋንጫዎችን ያነሱ የመጀመሪያው አሰልጣኝ ሆነዋል።
#ethiopianbroadcastingcorporation #soccer #astonvilla #uefa #europa #league

1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.