በአፋር ክልል የማሕበረሰቡን ህይወት የሚያሻሽሉ የመንገድና የድልድይ ፕሮጀክቶች…
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ደ/ር) እና የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ በክልሉ የተገነቡ የመንገድና የድልድይ ፕሮጀክቶችን መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል።
ፕሮጀክቶቹ ከ433 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸውና ሚኒስቴሩ በቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የገነባቸው መሆኑ ተገልጿል።
ከተመረቁ ፕሮጀክቶች መካከል የገቢ ረሱ እና የሀሪ ራሱ ዞኖችን የሚያገናኘው የ64 ኪሎ ሜትር የጠጠር መንገድ እና በውስጡ የያዘው የብረት ድልድይ አንዱ ሲሆን÷ ከ81 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግና 361 ሚሊየን ብር ወጪ የተደረገበት መሆኑ ተመላክቷል።
ፕሮጀክቱ የክልሉን ዞን ሦስት እና ዞን አምስት እንዲሁም የአማራ ክልልን ከአፋር ክልል በማገናኘት የሕዝቡን እንግልት በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚቀንስም ተገልጿል።
64 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው ከገለዓሎ ሰሙሮቢ የመንገድ ፕሮጀክት የአካባቢውን ማህበረሰብ የ50 ዓመታት ጥያቄ የመለሰና በሁለቱ ዞኖች የሚገኙ ሕዝቦችን ያገናኘ መሆኑም ተጠቁሟል።
ሌላኛው ፕሮጀክት የሀደለኤላ እና ሰሙሮቢ ወረዳዎችን የሚያስተሳስረው የ18 ኪሎ ሜትር የጠጠር መንገድ እና በዚሁ መስመር የተገነባው የአሬሶ ድልድይ በዛሬው ዕለት ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል።
በ72 ሚሊየን ብር በጀት የተሰራው ይህ ፕሮጀክት÷ ከ16 ሺህ በላይ ዜጎችን ከወረዳና ከዞን ማዕከላት ጋር በማገናኘት የሕዝቡን የኑሮ እንቅስቃሴ ያቀላጥፋልም ነው የተባለው።
በክልሉ በቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት አማካኝነት የተሠሩ የመስኖ ግድብ፣ የንጹህ መጠጥ ውሃ እና የእንስሳት ውሃ ፕሮጀክቶች በትናንትናው ዕለት ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል፡፡
በምንተስኖት ሙሉጌታ

15 days ago