Logo
FastMereja
ቶሚ ፊትነስ ሴንተር ለአገራችን አዲስ የሆነውን “ፒላቲዝ” ስፖርት ስቱዲዮ በይፋ ከፈተ!
#fastmereja I በኢትዮጵያ የፊትነስ ዘርፍ በርካታ ስራዎችን በመስራት የሚታወቀው ቶሚ ፊትነስ ሴንተር፣ በመላው ዓለም ከፍተኛ ተወዳጅነትና ውጤታማነትን ያስመዘገበውን፣ ለአገራችን ደግሞ አዲስ የሆነውን “ፒላቲዝ” (Pilates) ስፖርት ስቱዲዮ በቦሌ ዮድ አቢሲኒያ አካባቢ በይፋ መክፈቱን አስታወቀ።

የድርጅቱ መስራችና ባለቤት አቶ ቶማስ ሀይሉ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደተናገሩት፣ ማዕከሉ ለአገራችን አዲስ የሆኑ የሰውነት ማጠናከሪያ፣ የአቋም ማስተካከያና ከጉዳት ማገገሚያ ዘመናዊ የስፖርት አይነቶችን ይዞ መቅረቡን ገልጿል።

አቶ ቶማስ ሀይሉ አክለውም፣ ይህ አዲስ ስቱዲዮ በውጭ ሀገር ከፍተኛ ልምድና እውቀት ያላቸውን ፕሮፌሽናል አሰልጣኞች ያካተተ መሆኑን ገልጸው፣ የሚሰጡት አገልግሎቶች እጅግ ዘመናዊና የቅንጦት (Luxury) ቢሆኑም፣ የተቀረጸው የዋጋ ተመን ግን የህብረተሰቡን አቅም ያገናዘበና ተመጣጣኝ (Affordable) መሆኑን አስረድተዋል።

ይህ የስፖርት አይነት እንቅስቃሴዎችን በጥንቃቄ በመቆጣጠር የሰውነት ጥንካሬን፣ የመተጣጠፍ ብቃትን፣ የፖስቸር(የአቋም) መስተካከልን እና ትክክለኛ አተነፋፈስን ለማሳደግ ታስቦ የተዘጋጀ ነው።

አዲሱ ስቱዲዮ የሆድና የጀርባ ጡንቻዎችን ለማዳበር፣ የሰውነት ቅርጽን ለማስተካከል እንዲሁም ከጀርባ ህመም፣ ከቀዶ ጥገና እና ከመገጣጠሚያ ጉዳቶች በፍጥነት ለማገገም የሚረዱ ዘመናዊ አገልግሎቶችን ያካተተ መሆኑ ነዉ የተገለፀዉ።

ስቱዲዮው ከሚሰጣቸው ልዩ ልዩ አገልግሎቶች መካከል "ሪፎርመር" የተባለውን አልጋ መሰል ማሽን በመጠቀም ሁሉንም የሰውነት ክፍሎች የሚያሰራው ሪፎርመር ፒላቲስ፣ ከ35 እስከ 40 ዲግሪ ሴንቲግሬድ በሆነ ሙቀት ባለው ክፍል ውስጥ የሚሰራው "ሆት ፒላቲስ"፣ አፍሪካን መሰረት ያደረገውና ለውጥረት መቀነሻ የሚጠቅመው "ኬሜቲክዮጋ" እንዲሁም ለነፍሰጡር እናቶች ተብሎ የተዘጋጀው "የነፍሰጡር ዮጋ (Prenatal Yoga)" ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

ማዕከሉ መደበኛና ሙሉ ሥራውን ከመጪው ሰኞ ጀምሮ በይፋ የሚጀምር በመሆኑ፣ ፍላጎት ያላቸው ደንበኞች በቦታ እጥረት እንዳይቸገሩ ቀድመው መመዝገብና ቦታ መያዝ እንደሚችሉ ጥሪ ቀርቧል።

16 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.