ምርጫው ተዓማኒ እንዲሆን መገናኛ ብዙኃን ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ ነው - ወ/ሮ እናትዓለም መለሰ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ፍትሃዊና ተዓማኒ እንዲሆን መገናኛ ብዙኃን ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ ነው አሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናትዓለም መለሰ።
“ለዴሞክራሲያዊ ምርጫ ስኬት የመገናኛ ብዙኃን ሚና” በሚል መሪ ሐሳብ የተዘጋጀ የውይይት መድረክ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
ሚኒስትሯ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ሐሳባቸውን በነፃነት እንዲያንሸራሽሩ በማድረግና ሕዝብን ከፓርቲዎች ጋር በማገናኘት መገናኛ ብዙኃን ድልድይ ሆነው እያገለገሉ ነው።
መረጃዎችን በመፈተሽ፣ የደፈረሰ ሐሳብን በማጥራት እና በማቃናት ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አላቸው ብለዋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እና የኢትዮጵያ ሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በጋራ ባዘጋጁት መደረክ ላይ የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን የሥራ ኃላፊዎች እና ጋዜጠኞች ታድመዋል።
በአመለወርቅ መኳንንት

15 days ago