(ዘ-ሐበሻ ዜና) የትራምፕ አማካሪ አሜሪካ በምስራቅ አፍሪካ ላይ ያላትን አቋም በይፋ ገለፁ፡፡ የፕሬዝደንት ትራምፕ የአረብና አፍሪካ ጉዳዮች ከፍተኛ አማካሪ የሆኑት ማሳድ ብሉስ በትላንትናው እለት ከተለያዩ ሚዲያዎች ጋር ቃለምልልስ አድርገዋል፡፡ ይህንን አስመልክተው በኤክስ ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት መልእክት ‹‹ከአልጀዚራ፣ አልአረቢያና ከስካይ ኒውስ አረቢያ ቻናሎች ጋር ቃለምልልስ በማድረጌ ደስታ ተሰምቶኛል፡፡›› በማለት ጀምረው በእነዚህ ቃለምልልሶች ያነሷቸውን ነጥቦች ዘርዝረዋል፡፡ ከ
እነዚህ ጉዳዮች መካከል በመጀመሪያ የጠቀሱት የሱዳንን ሁኔታ ሲሆን ፕሬዝደንት ትራምፕ የተባባሰው ሰብአዊ ቀውስ ለመፍታት ፍላጎት እንዳላቸው ማስረዳታቸውን ገልፀዋል፡፡ በበርሊን በተካሄደውና 22 አገራትና አለም አቀፍ ድርጅቶች በደገፉት ለሱዳን ግጭት ሰላማዊ መፍትሄ ለማምጣት በተቀረፀው ማእቀፍ ላይ አፅንኦት መስጠታቸውን የተናገሩት ማሳድ ብሉስ ጨምረውም ‹‹የሰብአዊነት ተኩስ አቁም እንዳይደረግ እንቅፋት የሚፈጥሩትንና ለሁለቱም ተፋላሚዎች ወታደራዊ ድጋፍ የሚሰጡ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስባለሁ›› ብለዋል፡፡ ለሱዳን ዘላቂ ተኩስ አቁም እንደሚያስፈልጋትና በሱዳናዊያን መካከል ሁሉን ያሳተፈ ውይይት ተደርጎ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር እንዲደረግም ጠይቀዋል፡፡
ማሳድ ብሉስ በማስከተል እንደገለፁት በእነዚህ ቃለምልልሶቻቸው የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስን ጉብኝት አስመልክተው ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በአሜሪካና ኢትዮጵያ የሁለትዮሽ ውይይት ላይ መሳተፋቸውን የገለፁት አማካሪው ከዚህ ጎን ለጎን በተለያየ ጉዳይ ላይ ውይይት መካሄዱን አስታውቀዋል፡፡ ከእነዚህ መካከልም በአባይ ወንዝ ላይ ሁለቱም አካላት ስምምነት ላይ እንዲደርሱ ፕሬዝደንት ትራምፕ የሚፈልጉ መሆኑ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የተገለፀላቸው መሆኑን ጠቅሰው በቀጠናው መረጋጋትን ለማስፈን ድጋፍ በመስጠት ላይ ውይይት መደረጉንም አስረድተዋል፡፡

17 days ago