Logo
FBC
ኢትዮጵያ በምግብ ምርት ራሷን እንድትችል ታሪክ ቀያሪ ሥራዎችን እየሠራን ነው፡፡ ግብርናን በማስፋት፣ ምርምሮችን በመደገፍ፣ ቴክኖሎጂዎችን በማላመድና ፈጠራዎችን በማበረታታት የፖሊሲና የለውጥ ርምጃዎች በሰፊው እየወሰድን እንገኛለን፡፡ የግብርናውን ዘርፍ ከዲጂታል፣ ከምሕንድስና ቴክኖሎጂዎችና ከባዮቴክኖሎጂ ጋር ለማጣጣም እየታገልን ነው፡፡ የግብርና ኢንቨስትመንትን ማጎልበት የሠርክ ሥራችን ሆኗል፡፡ ለዘላቂ ምርትና ምርታማነት ዕድገት የሚረዱ የተሻሻሉ ግብዓቶችንና የሀብት አጠቃቀምን ማሳደግ ከሁሉም ሥራችን የምናስቀድመው ነው፡፡ በዚህም የኢትዮጵያን ግብርና በሚቀጥሉት ዐሠርት ዓመታት ፈጣን እመርታዊ ለውጥ እናረጋግጣለን፡፡

የመደመር መንግሥት ገጽ 178

1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.