Logo
SeledaPost
ኤርትራ እና ግብጽ የባሕር ትራንስፖርት ትብብር ስምምነት ተፈራረሙ።

ስምምነቱ የተፈረመው፤ የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ባደር አብደላቲ እና የትራንስፖርት ሚንስትር ካሜል አል ዋዚር ትናንት በአሥመራ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት መሆኑን የግብጽ የዜና ምንጮች ዘግበዋል።

ስምምነቱ፣ የሁለቱን አገራት ወደቦች በባሕር ትራንስፖርት በማስተሳሰር የንግድ ግንኙነቱን ለማጠናከር ያለመ መሆኑን ዘገባዎቹ ጠቅሠዋል።

ግብጽ፣ በባሕርና ባቡር ሐዲድ ትራንስፖርት እንዲሁም በወደብ አስተዳደር ዙሪያ ለኤርትራ ልምዷን ለማጋራት መስማማቷንም ዘገባዎቹ አመልክተዋል።

በግብጹ ልዑካን ቡድን የተካተቱ ባለሀብቶች፣ ኤርትራ ውስጥ በማዕድን፣ ትራንስፖርት፣ መድሃኒት እና አሳ ልማት ዘርፍ መሠማራት በሚችሉበት ሁኔታ ዙሪያ ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቅ ጋር መወያየታቸውም ተገልጧል።

seledadotio
seledadotio
18 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.