የባሕረ ሰላጤው ሀገራት በኢራን ላይ ጠንካራ ማዕቀብ እንዲጣል የሚጠይቅ የውሳኔ ሃሳብ ለተመድ አቀረቡ
****************
የባሕረ ሰላጤው ሀገራት በሆርሙዝ ሰርጥ የመርከቦች የደኅንነት ስጋትን ለመቅረፍ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጣልቃ ገብቶ አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስድ ጥሪ አቅርበዋል።
የቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ኢራን በዓለም አቀፍ የንግድ መርከቦች ላይ የምታደርሰውን ጥቃት ካላቆመች እና የጣለችውን ሕገ-ወጥ ቀረጥ ካላነሳች እንዲሁም የቀበረቻቸው የባሕር ውስጥ ፈንጂዎች ያሉበትን ቦታ ይፋ ካላደረገች ጠንካራ ማዕቀብ እንዲጣልባት እና ሌሎች እርምጃዎች እንዲወሰዱባት ይጠይቃል።
የኳታር፣ የባሕሬን እና የተባበሩት ዓረብ ኢምሬት ከፍተኛ ዲፕሎማቶች፣ በፋርስ ባሕረ ሰላጤ የንግድ እንቅስቃሴው ከጦርነቱ በፊት ወደነበረበት መመለስ እንዳለበት አፅንዖት ሰጥተዋል።
አሜሪካ የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ በመደገፍ የባሕር ላይ የንግድ ነፃነት መከበር እንዳለበት ስታሳስብ፣ ኢራን በበኩሏ ለአካባቢው አለመረጋጋት እና ለተፈጠረው ግጭት የአሜሪካን ወታደራዊ እንቅስቃሴ ተጠያቂ ታደርጋለች።
በቢታንያ ሲሳይ
#middleeast #persiangulf #gulfstates #un #ebc

1 month ago