አሜሪካ በኢራን ላይ ስታካሂድ የነበረውን ወታደራዊ ዘመቻ ማጠናቀቋን አስታወቀች
#ethiopia | የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ማክሰኞ ዕለት በዋይት ሀውስ በሰጡት መግለጫ፣ ዩናይትድ ስቴትስ በኢራን ላይ ከፍታው የነበረው ወታደራዊ የማጥቃት ዘመቻ ግቡን በመምታቱ መጠናቀቁን ይፋ አድርገዋል።
የካቲት 21 ቀን 2018 ዓ.ም የተጀመረውና “ኦፕሬሽን ኢፒክ ፉሪ” የተሰኘው ይህ ዘመቻ መገባደዱን ያረጋገጡት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፤ "የዘመቻችንን ዓላማዎች አሳክተናል፤ አሁን የሰላምን መንገድ እንመርጣለን። ፕሬዚዳንቱም ከስምምነት ላይ ለመድረስ ጽኑ ፍላጎት አላቸው" ሲሉ ተናግረዋል።
ይሁን እንጂ የሆርሙዝ ወሽመጥን የንግድና የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ዳግም ለማስጀመር ያለመ አዲስና አነስተኛ ዘመቻ ሰኞ ዕለት መጀመሩን አቶ ሩቢዮ አክለው ገልጸዋል። ይህ አዲሱ እንቅስቃሴ ከመጀመሪያው መጠነ ሰፊ ጦርነት የተለየ መሆኑን የጠቆሙት ሚኒስትሩ፣ አሜሪካ ቀዳሚ ጥቃት ካልተሰነዘረባት በቀር በራሷ አነሳሽነት ወታደራዊ እርምጃ እንደማትወስድ አስጠንቅቀዋል።
የዚህ ወታደራዊ ዘመቻ ዋነኛ መነሻ ኢራን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ እንዳታመርት ለማስቆም ያለመ እንደነበር ይታወቃል። ይሁንና አሜሪካ ዘመቻው ተጠናቋል ብትልም፣ እስካሁን ድረስ የኢራንን 408 ኪሎ ግራም በከፍተኛ ደረጃ የበለጸገ ዩራኒየም ማስወጣትም ሆነ የሆርሙዝ ወሽመጥን ለመርከቦች እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ ክፍት ማድረግ እንዳልቻለች መረጃዎች ያመለክታሉ።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu
#አሜሪካ #ኢራን #ማርኮ_ሩቢዮ #ዓለምአቀፍ_ዜና #የውጭ_ግንኙነት #ፖለቲካ #የሆርሙዝ_ወሽመጥ #ዜና

5 months ago