የላብ አድዋ፡- አዲሱ አርበኝነት
****************
የኢትዮጵያ ታሪክ በጽናትና በጀግንነት የወርቅ ቀለም የተጻፈ መጽሐፍ ነው። አባቶቻችንና እናቶቻችን ሀገርን በክብር አቆይተውልናል።ትናንት አርበኝነት ማለት በጫካና በዱር ለነፃነት መውደቅ፣ በደምና በአጥንት ድንበር ማስከበር ነበር። ዛሬ ግን የታሪክ የሩጫ ቅብብል በትውልዱ እጅ ገብቷል፤ የዛሬው አርበኝነት ግንባሩ ተቀይሯል፣ ጠላቱም መልክ ለውጧል። ዛሬ አርበኝነት ማለት ለሀገር ብልጽግና መቆም፣ ድህነትንና ድንቁርናን ድል ማድረግ ነው።
ታሪክን መዘከር የትናንትን ድል ለማውራት ብቻ ሳይሆን ለነገው ጉዞ ስንቅ ለመሰብሰብ ነው። የአድዋ ድል መታሰቢያና የአብርሆት ቤተ-መጻሕፍት ዝም ብለው የድንጋይና የሲሚንቶ ክምር ህንፃዎች አይደሉም። እነርሱ የኢትዮጵያዊነት ጽናትና የጥበብ ጥማት ህያው መገለጫዎች ናቸው።
"ከታሪክ ያልተማረ፣ ለታሪክ አይበቃም" እንደሚባለው እነዚህ መዘክሮች ወጣቱ ትውልድ የትናንቱን ነፃነት እንዲዳስሰው፣ ዛሬን ደግሞ በኩራት እንዲተነፍሰው የሚያስችሉ የንቃተ-ህሊና ማዕከላት ናቸው።
በ21ኛው ክፍለ ዘመን ሉዓላዊነት የሚረጋገጠው በጠመንጃ አፈሙዝ ብቻ አይደለም። እውነተኛ ሉዓላዊነት የሚለካው በምግብ ራስን በመቻል፣ በኢንዱስትሪ ብቃትና በዲጂታል ቴክኖሎጂ ልዕልና ነው።
ትናንት በጠብመንጃ ድንበር ይከበር ነበር፤ ዛሬ ግን የሉዓላዊነት ድንበራችን የስንዴ ማሳዎቻችን፣ የፋብሪካዎቻችን ጭስና የዲጂታል ቴክኖሎጂ ኮዲንግ ብቃታችን ነው። ከእርዳታ ጠባቂነትና ከተመፅዋችነት ሰንሰለት ተላቆ ወደ ስንዴ ላኪነት መሸጋገር፣ የዘመናችን ሌላው "የአድዋ ድል" ተደርጎ ሊወሰድ የሚገባው የኢኮኖሚ ነፃነት አዋጅ ነው።
ታላቁ የህዳሴ ግድብ የአዲሱ አርበኝነታችን ትልቅ ማኅተም ነው። ዓለም አቀፍ ጫናዎችንና የዲፕሎማሲ አዙሪቶችን ተቋቁመን፣ ከራስ ጉርስ ቀንሰን የዓባይን ውሃ መገደብ መቻላችን "እምቢኝ ለጭቆና" የሚለው የጥንት መንፈሳችን በዘመናዊ ምህንድስና መገለጡን ያሳያል። ከዚህም በተጓዳኝ፣ ኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄዋን በዲፕሎማሲና በጋራ ተጠቃሚነት መርህ ለማሳካት የምታደርገው ጥረት፣ የህልውናችንና የኢኮኖሚ ነፃነታችን ዋስትና ነው።
የብሪክስ አባልነትና የኮሪደር ልማት ሥራዎች ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ መድረክ ቀና ብላ እንድትቆም እያደረጓት ነው። ከተሞቻችንን ለኑሮ ምቹ ማድረግና ቱሪዝምን ማስፋፋት የሀገር ፍቅር ተግባራዊ መግለጫዎች ናቸው።
ይሁን እንጂ፣ እነዚህ ሁሉ ልማቶችና ዲፕሎማሲያዊ ስኬቶች ዘላቂ ትርጉም የሚኖራቸው በውስጣችን ሰላምና አንድነት ሲሰፍን ብቻ ነው። የአባቶቻችን አንድነት በጠላት ፊት የነበረውን አሸናፊነት፣ እኛ ዛሬ በጠረጴዛ ዙሪያ ውይይትና በሀገራዊ ምክክር ልንደግመው ይገባል። የልዩነት ግንቦችን አፍርሰን በሀገራዊ ስምምነት ካልተሳሰርን፣ ድህነት የሚባለውን የጋራ ጠላታችንን ማሸነፍ አንችልም።
አርበኝነትን ከአውድማ ወደ ፋብሪካ፣ ከዱር ወደ ላቦራቶሪ፣ ከጠመንጃ ወደ ኮዲንግ (Coding) የምናሸጋግርበት ጊዜ አሁን ነው። አባቶቻችን በደማቸው የጻፉትን ነፃነት፣ እኛ በላባችንና በእውቀታችን ቀለም እናድምቀው።
ኢትዮጵያዊነት ፈተናን ወደ ዕድል የመቀየር ጥበብ ነውና የትናንቱ የድል መንፈስ ዛሬም በሥራችን ውስጥ ይንገሥ!

1 month ago