(ዘ-ሐበሻ ዜና) የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ ሀገራቸው በጀርመን ካሰፈረቻቸው ወታደሮች ውስጥ ቀደም ሲል በፔንታጎን ከተገለጸው እቅድ በላይ በርካታ ወታደሮችን እንደምታስወጣ አስታወቁ። ፕሬዝዳንቱ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ "የወታደሮቻችንን ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እንቀንሳለን፤ የምናስወጣውም ከ5 ሺህ ወታደሮች እጅግ የላቀ ይሆናል" ያሉ ሲሆን፣ ስለ አፈጻጸሙ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ግን ተቆጥበዋል።
የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ቃል አቀባይ በበኩላቸው፣ ህብረቱ በዚህ የዋሽንግተን ውሳኔ ዙሪያ ተጨማሪ ማብራሪያና መረጃ ከአሜሪካ መንግስት እየጠበቀ መሆኑን አረጋግጠዋል። ይህ የአሜሪካ የጦር ሰራዊት ቅነሳ ውሳኔ የተሰማው፣ የጀርመኑ ቻንስለር ፍሬድሪክ ሜርዝ "ኢራን በድርድሩ የትራምፕን አስተዳደር እያዋረደችው ነው" የሚል ጠንካራ ትችት መሰንዘራቸውን ተከትሎ መሆኑን ዘገባው አመልክቷል።

5 months ago