የምርጫውን ዕለት በጉጉት እየጠበቅን ነው - የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች
******************
የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን የመራጭነት ምዝገባ በንቃት እያካሄዱ ነው።
ተማሪዎቹ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ያመቻቸውን ልዩ የምዝገባ ጊዜ በመጠቀም፣ በበይነ መረብ (Online) አማካኝነት ለመራጭነት የሚያስችላቸውን ምዝገባ እያከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል።
ለተማሪዎችና ለተወሰኑ የማኅበረሰብ ክፍሎች በልዩ ሁኔታ የተፈቀደውን የምዝገባ ጊዜ በመጠቀም፣ የሚመለከታቸው ዜጎች ሁሉ ከወዲሁ ተመዝግበው ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን እንዲጠቀሙ ተማሪዎቹ ጥሪ አቅርበዋል።
የምርጫ ዕለቱን በጉጉት እየጠበቁ መሆኑን የሚናገሩት ተማሪዎቹ፣ ሌሎችም የተጨመረውን አጭር የምዝገባ ጊዜ በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባ አሳስበዋል።
የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ኅብረት ፕሬዝዳንት ተማሪ መልካሙ መላኩ እንደገለጸው፣ ሁሉም ተማሪዎች በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተሰጠውን ዕድል ተጠቅመው እንዲመዘገቡ ኅብረቱ የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን በመሥራት ላይ ይገኛል።
ይህ ዲጂታል የምዝገባ አማራጭ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ሳይለዩና ብዙ ሳይደክሙ መብታቸውን እንዲጠቀሙ ትልቅ ዕድል መፍጠሩም ተመልክቷል።
በጀማል አህመድ
#assosauniversity #voterregistration #digitaldemocracy #nebe #studentparticipation

5 months ago