Logo
YenetaTube
አሜሪካ ድጋፍ ባልሰጡ የኔቶ አባል ሀገራት ላይ ማዕቀብ ለመጣል ማቀዷ ተገለጸ

የዩናይትድ ስቴትስ መከላከያ ሚኒስቴር በኢራን ጦርነት ወቅት ድጋፍ አላደረጉም ባላቸው የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት ኔቶ አባላት ላይ ሊወሰዱ የሚችሉ የቅጣት እርምጃዎችን የሚያመለክት የውስጥ ሰነድ ይፋ ማድረጉን አንድ የአሜሪካ ባለሥልጣን ለሮይተርስ ገልፀዋል።

በእነዚህ የፖሊሲ አማራጮች ውስጥ የተካተቱት ዋና ዋና ነጥቦች ውስጥ የአባልነት ዕግድን በተመለከተ ስፔንን ከመሰሉ አባል ሀገራት ጋር ያለውን ግንኙነት በማገድ ረገድ የተያዘ እቅድ መኖሩ ተገልጿል።

ብሪታንያ በፎክላንድ ደሴቶች ላይ ባላት የይገባኛል ጥያቄ ዙሪያ አሜሪካ የነበራትን ዲፕሎማሲያዊ ድጋፍ በድጋሚ መገምገምንም ያካትታል።

በኔቶ መዋቅር ውስጥ "አስቸጋሪ" ተብለው የተፈረጁ ሀገራት ከሚይዟቸው ቁልፍ እና ከፍተኛ የኃላፊነት ቦታዎች እንዲወገዱ ማድረግ ሌላኛው ጉዳይ ነው።

እንደ ባለሥልጣኑ ገለጻ፥ሰነዱ በከፍተኛ የፔንታገን የሥልጣን እርከኖች ላይ እየተመከረበት ያለ ሲሆን፤ ዋነኛው የቅሬታ ምንጭ የተወሰኑ ሀገራት ለአሜሪካ ጦር የግዛት መዳረሻ፣ የጦር ሰፈር እና የአየር ክልል አጠቃቀም ፈቃድ ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆናቸው ነው።

ይህ ትብብር ለማንኛውም የኔቶ አባል ሀገር "ዝቅተኛው የጋራ ግዴታ" መሆኑን ያሰምርበታል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።

ሳራ ዮሐንስ

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.