Logo
SeledaPost
የኢራን መርከቦች አሜሪካ በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ በጣለችው እገዳ አቅራቢያ ከመጡ "ይደመሰሳሉ" - ትራምፕ

በዋሽንግተን እና በቴህራን መካከል የተደረገው ውይይት መክሸፉን ተከትሎ፣ የአሜሪካ ማዕከላዊ ኮማንድ የዶናልድ ትራምፕን መመሪያ ተግባራዊ በማድረግ ከዛሬ ማለዳ ጀምሮ በሆርሙዝ ውሽመጥ ላይ እገዳ መጣል ጀምሯል።

​ትራምፕ ከቴህራን ጋር የሁለት ሳምንት የተኩስ አቁም ስምምነት ማድረጋቸውን ካወጁ በኋላ፣ ኢራን እና አሜሪካ ቅዳሜ ዕለት በኢስላማባድ ውይይት አድርገው ነበር። ነገር ግን እሁድ ዕለት የአሜሪካ ልዑካን ቡድን መሪ ጄዲ ቫንስ ምንም ዓይነት ስምምነት ላይ አለመደረሱን ገልጸዋል። በመቀጠልም ትራምፕ የአሜሪካ ባህር ኃይል በባህር ሰርጡ ላይ እገዳ እንዲጥል እና ወሽመጡ ለማለፍ ለኢራን የጉዞ ቀረጥ የሚከፍሉ ማናቸውንም መርከቦች እንዲያስቆም ትዕዛዝ አስተላልፈዋል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያ

seledadotio
seledadotio
2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.