Logo
YenetaTube
በመስቀሉ ሰላም አደረገ - ቄጤማ ይዘን የምስራች እንባባላለን🙏

አዳም ከ5500 ዘመን በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለው ባለው ቃል መሠረት ዘመን እየቆጠረ ቀኑን ሲጠብቅ ቆየ፡፡ በዕለተ አርብ ልክ ክርስቶስ ነብሱን ከስጋው ሲለይ፣ አዳም እንደ ተስፋ ቃሉ ይመጣልና በፀሎት እናስታውሰው ብሎ ልክ 11:00 ላይ በሲኦል ያሉትን ነብሳት “ተንስኡ ለጸሎት ለጸሎት ተነሱ” አላቸው፡፡ እነርሱም “እግዚኦ ተሰሀለነ፣ አቤቱ ይቅር በለን” ብለው መለሱ፡፡ ወዲያው ጌታችን “ሰላም ለኩልክሙ፣ ሰላም ለሁላችሁ ይሁን” አላቸው፡፡ እነርሱም “ምስለ መንፈስከ፣ እንደ ቃልህ ይደረግልን” አሉት፡፡ ሲኦል ባዶ ሆነች፣ ነፍሳትን ሁሉ ነጻ አወጣ፡፡ በማግስቱ ልዩዋ ቅዳሜ፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመቃብር ያሳለፋት፣ የምትጾም ከመጾም አልፋ የሚከፈልባት ነችና ቀዳም ሥዑር ትባላለች፡፡ ለምለም ቅዳሜ፣ ቅዱስ ቅዳሜም ትባላለች፡፡

እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያምና ወዳጆቹ ሐዋርያት ትንሣኤውን እስኪያዩ በሐዘን፣ በጾም፣ በጸሎት ቆይተዋልና እኛም በአክፍሎት፣ በጾም እናሳልፋታለን። በቀዳም ሥዑር ሌሊት ሥርዓቱ የሚጀመረው በመኀልየ መኃልይ ዘሰሎሞን ምንባብ ነው፡፡ ማኀሌቱም እዝሉ እየተቃኘ እየተመጠነ፣ እየተዘመመ እየተመረገደ እየተጸፋ ያድራል፡፡ ጠዋት ላይ አቡን መዋሥዕት ውዳሴ ማርያም ዜማ ይደረሳል፡፡ ልብሰ ተክህኖ የለበሱ ካህናትና ዲያቆናት ቄጤማ ተሸክመው ቃጭል ሲያቃጨሉ መታየታቸው ዕለተ ትንሣኤውን ለሚናፍቅ ምእመን ትልቅ ብስራት ነው፡፡ ነፍሳት ከሲኦል ወጡ፡፡ የገነት በር ተከፈተልን፣ ርስተ መንግስተ ሰማያት ተመለሰልን፤ አባታችን አዳምም ከፈጣሪው ጋር ታረቀልን በማለት “በመስቀሉ ሰላመ አደረገ” እያልን የተድላ፣ የደስታ ምልክት የሆነ ልምላሜ ያለውን ቄጤማ ይዘን የምስራች እንባባላለን፡፡

በኖኅ ጊዜም ርግብ “የጥፋት ውኃ ጎደለ፣ አለቀ እያለች “የወይራ ዝንጣፊ” ይዛ ኖኅን አብስራዋለች፡፡ ርግብ የካህናት፣ ኖኅ የምእመናን፣ ኖኅ እጁን ዘርግቶ ርግብን እንደተቀበላት ካህናትም በየመንደሩ እየዞሩ “ክርስቶስ ተመረመረ፤ ዲያብሎስ ታሰረ” በማለት ቄጤማ ሲያድሉ፤ ምእመናንም እጃቸውን ዘርግተው መቀበላቸው የዚህ ምሳሌ ነው፡፡ ስለዚህ አሁንም ቢገኝ የወይራ ልምላሜ፣ ቢታጣ ቄጠማ እየታደልን የምሥራች መባባላችን ነፍሳት ከሲኦል ለመውጣታቸው መታሰቢያ ነው፡፡ ይህን የድኅነታችንን ብስራት በደስታ የሚቀበሉት ገዳማውያን የማዳኑን ሥራ፣ ፍቅሩን ዘወትር ለማሰብ ዓለምን ትተው ወጥተዋልና ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና ከበረከታቸው እንካፈል፡፡

ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.