ምንም ጥፋት አላገኘሁበትም፤ እናንተ ወስዳችሁ እንደ ሕጋችሁ ፍረዱበት🙏
ከኢየሩሳሌም በስተምሥራቅ የሚገኘው ደብረ ዘይት ተራራ መካከል የቄድሮን ሸለቆ ከግርጌውም ጌቴ ሴማኔ የተባለው የአትክልት ስፍራ አለ። በጸሎተ ሐሙስ ምሽት ጌታችን የጸለየበት በኋላም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስታርፍ ቅዱስ ሥጋዋ የተቀበረበት ነው። ይሁዳም ስፍራውን ስለሚያውቀው የካህናት አለቆችን፣ ጭፍሮችን፣ ፈሪሳውያንና ሌሎች ፋና ጋሻ ጦርም የያዙትን አስከትሎ መጣ፡፡ ቀርቦም “መምህር ሆይ ቸር ውለሃል፤ ሰላም ላንተ ይሁን” ብሎ ሳመው፡፡ ጌታችንም “የሰውን ልጅ በመሳም አሳልፈህ ትሰጠዋለህን?” አለው፡፡ ከያዙት ሰዓት አንሥቶ አይሁድ ከቀያፋ ወደ ሐና፣ ከሐና ወደ ቀያፋ ሲያመላልሱት አደሩ፡፡ ቅዱስ ማቴዎስ 27÷1-57 እንደተጻፈው ሲነጋ በሦስት ሰዓት ከቀያፋ ወደ ጲላጦስ አደባባይ አስረው ወሰዱት፡፡ አይሁድ ይህን አጥፍቶአል የሚሉት ነጥብ ሳይኖራቸው ነውና ጌታችንን ለፍርድ ያቀረቡት ጲላጦሰ ወደ ተሰባሰቡበት ቦታ ወጥቶ “ይህን ሰው ወደ እኔ ያመጣችሁበት በደል ምንድን ነው?” ሲል በጠየቃቸው ጊዜ በቂ ምላሽ አላቀረቡም፡፡
ይልቁንም በዮሐንስ 18÷28-31 ተጽፎ እንደምናገኘው “ክፉ የሠራ ባይሆንስ ወደ አንተ ባላመጣነውም ነበር” በሚል የሸፍጥ ቃል አጉረመረሙ፡፡ ጲላጦስ መልሶ “እኔ ምንም ጥፋት አላገኘሁበትም፤ እናንተ ወስዳችሁ እንደ ሕጋችሁ ፍረዱበት፤” አላቸው፡፡ አይሁድም ኦሪት “ጻድቁን ሰው አትግደል፤ ኀጥኡንም ከፍርድ አታድን፤” ትላለችና እኛስ ማንንም ልንገድል አልተፈቀደልንም፤ ብለዋል፡፡ ይኸውም መንፈስ ቅዱስ “በሕጋችን ጻድቀ ባሕርይ ክርስቶስን መግደል አይገባንም ሙሉ በሙሉ ጥፋተኞች ነን፤” ሲያሰኛቸው ነው፡፡ ለፋሲካ በዓል አንድ እስረኛ ይፈታላቸው ነበርና ኢየሱስን ልፍታው ሲላቸው፤ ሰው ገድሎ የጣሰረውን ወንበዴ በርባንን ፍታልን ኢየሱስን ግን ስቀለው እያሉ ጮኹ፡፡ ሕዝቡም ስቀለው… ስቀለው… እያሉ ይጮሁ ነበር፡፡ በኋላም ከዚህ ሰው ደም ንጹህ ነኝ ብሎ እጁን ታጥቦ እንዲሰቅሉት አሳልፎ ሰጣቸው፡፡ እርሱ ሞቶ ዓለም እንዲድን መጥቷልና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያለ ጥፋቱ ሞት ተፈረደበት፡፡ ስለዚህም ገርፈው ሰቀሉት፡፡ ለአዳም በገባለት ቃል ኪዳን መሠረት፤ ትንቢቱም ይፈጸም ዘንድ መከራን ተቀበለ፡፡
ጲላጦስ በሦስት ሰዓት ይሰቅል ዘንድ ሲፈርድበትም፤ መስቀሉንም ተሸክሞ በዕብራይስጥ ጎልጎታ ወደ ተባለው፣ የአዳም ዐጽም ወደተቀበረበት ቀራንዮ ወደሚባል ቦታ ወጣ፡፡ ጌታችንም ከአዳም የራስ ቅል በላይ ሊያድነው መስቀል ተሸከሞ ተንገላታ፡፡ ቦታው በዮሐንስ 19÷20 “ለከተማ ቅርብ ነበረ” ሲባል እንዲሁም በዕብራውያን 13÷12 “ከበር ውጭ” መሆኑ ተመሰክሯል። አይሁድም የቀራንዮን ዳገት እየገረፉና እያንገላቱ አስወጥተው ጫፍ ሲደርሱ እጆቹን፣ እግሮቹን ደረቱንና ከወገቡ በታች በአምስት ችንካር ቸነከሩት፤ በዕለተ ዐርብ ቀትር 6 ሰዓት ላይም አይሁድ በዚያ በምድር መካከል ጌታችንን ሰቀሉት፡፡ እስከ ዘጠኝ ሰዓትም በምድር ላይ ጨለማ ሆነ፤ በ11 ሰዓትም ቅድስት ነፍሱ ከቅድስት ስጋው ተለየች፡፡ ስለዓለም መዳን አንዱ በፈቃዱ ሞተ፡፡ ይህን መስዋዕትነቱን ዘወትር የሚያስቡ ገዳማውያን ዓለምን ትተዋል፡፡ ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡
ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

2 months ago