የሕጽበተ እግር እና የጸሎተ ሐሙስ ሥነ ሥርዓት በድምቀት ተከናወነ
#ethiopia | የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ትሕትና በማሰብና የጸሎተ ሐሙስን በዓል በማስመልከት በመላው አገሪቱ በሚገኙ አድባራትና ገዳማት በመንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት ተከብሯል።
በአዲስ አበባ መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በተከናወነው በዚሁ ታላቅ መርሐ ግብር ላይ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ በተገኙበት የሕጽበተ እግር ሥነ ሥርዓት ተፈጽሟል።
በዕለቱም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያት እግራቸውን በማጠብ ያሳየውን ፍጹም ትሕትና ለማዘከር ብፁዕነታቸው የካህናትንና የዲያቆናትን እግር በውኃና በወይራ ቅጠል አጥበዋል።
ከመታጠቡ ሥነ ሥርዓት ጎን ለጎንም የዕለቱን ትርጉምና የድኅነት ጉዞ የሚያዘክሩ የጸሎት፣ የምህላና የስግደት መርሐ ግብሮች ሲከናወኑ ውለዋል።
በካቴድራሉ የተሰበሰቡ ምእመናንም የሕጽበተ እግሩን ሥርዓትና የማዕድ ምስጢር የታሰበበትን ቅዳሴ በመከታተል በዓሉን በጸሎት አሳልፈዋል።
በተለይም በዚህ ዕለት የሚፈጸመው ሥርዓተ ሕጽበትና የቅዳሴው ሥነ ሥርዓት አማናዊው የኪዳን መሠረት የተጣለበት መሆኑን በማሰብ፣ ካህናቱና ምእመናኑ በጾምና በጸሎት ተወስነው ለትንሣኤው በዓል መንፈሳዊ ዝግጅት እያደረጉ ይገኛሉ።
ጌትነት ተመስገን
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
📷 EOTC

6 months ago