ኢራን እና አሜሪካ የደረሱትን የተኩስ አቁም ስምምነት ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ ቀነሰ
የምጣኔ ሀብት ኢንተለጀንስ ክፍል ባልደረባ የሆኑት አሌክስ ሆምስ ለአልጀዚራ እንደተናገሩት ከገበያዎች የተሰባሰበው መረጃ የነዳጅ ዘይት ዋጋ ቀንሷል ፣ነገር ግን የታወጀው የተኩስ አቁም ስለመቆየቱ አንድ ሰው ብዙ እርግጠኛ መሆን አይችልም ብለዋል። ሆልምስ አክለው እንዳሉት “ስለዚህ ይህንኑ ለመከታተል ዋናው ቁልፍ ከእስራኤል ፣ ኢራን እና ሌሎች ወገኖች የሚመጡት ማንኛውም ምልክቶች ይህ የተኩስ አቁም ይቆይ እንደሆነ እናያለን” ብለዋል።
"በድርድር ላይ ትልቅ ክፍተት ስለሚኖር ገበያዎቹ አሁንም በመጠባበቅ ላይ ናቸው" ብለዋል። ምንም እንኳን ዋጋው መቀነሱ ግልጽ ቢሆንም የነዳጅ ዋጋ አሁንም በየካቲት መጨረሻ ከነበረው ጋር ሲነፃፀር በጣም ከፍ ያለ ነው። የሮይተርስ የዜና ወኪል እንደዘገበው በአሜሪካ ዌስት ቴክሴስ ገበያ የድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በበርሚል 16 በመቶ ገደማ ቀንሶ ወደ 94.59 ዶላር ደርሷል። የተኩስ አቁም ዜና ከተሰማ በኋላ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዋጋው በርሚል 15 በመቶ ቀንሶ ወደ 92.35 ዶላር አሽቆልቁሏል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በዩናይትድ ስቴትስ እና በኢራን መካከል ለሁለት ሳምንታት የሚቆይ የተኩስ አቁም ስምምነትን በደስታ እንደተቀበሉት ቃል አቀባያቸው ስቴፋን ዱጃሪች በመግለጫቸው አስታውቀዋል። ጉቴሬዝ ሁሉም ወገኖች "በአለም አቀፍ ህግ የሚጠበቅባቸውን ግዴታዎች እንዲወጡ እና የተኩስ አቁም ውሎችን እንዲያከብሩ በአካባቢው ዘላቂ እና ሁሉን አቀፍ ሰላም ለማምጣት መንገዱን እንዲጠርግ ጥሪ አቅርበዋል"።
seledadotio

2 months ago