ረቡዕ - የምክር ቀን፣ የመዓዛ ቀን፣ የዕንባ ቀን
ዕለተ ረቡዕ አይሁድ የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ይሙት ብለው የወሰኑበት ዕለት ነው። ዕለቱ “ዕለተ ምክር”፣ “ዕለተ መዓዛ” እና “ዕለተ አንብዕ” ይባላል፡፡ “ዕለተ ምክረ አይሁድ” ነው፡፡ ይህ ከሰኞው ምክር፣ ከማክሰኞውስ በምን ይለያል ቢሉ የአይሁድ አለቆች፣ ጸሐፍትና ፈሪሳውያን የተስማሙና እልባት ያገኙበት ስለነበር ነው፡፡ በመሃላቸው “ይህ ሰው ንጹሕ ነው፤ ሞት አይገባውም” የሚሉ ርቱዓን ስለነበሩ እዚህ ውሳኔ ላይ ለመድረስ ሦስት ቀን ፈጅቶባቸዋል፡፡ የሚበዙቱ ግን በክፋታቸው ስለጸኑ አቸንፈው መገደሉ ላይ ተስማሙ፡፡ ሌላኛው ጭንቀታቸው “እንግደልስ ብንል ምን ምስክር አለን፤ ሰውየው ንጹሕ ነው፤ ተፈትኖም ሐሰት አልተገኘበትም፤ የሚለው ነበር፡፡
የሐሰት ምስክሮችን ለማዘጋጀት ከወሰኑ በኋላ ግን ወዲያውኑ ለዚህ ጉዳይ ይጠቅሙናል ያሏቸውን ሰዎች በር ማንኳኳት ጀምረዋል፡፡ ታዲያ በዚህች እለት በሞቱ ላይ ቢስማሙም እንዴት እንደሚይዙት ቸግሯቸው፡፡ ወቅቱ “በዓለ ፋሲካ” በመሆኑ በየአገሩ ተበትነው የሚገኙ በርካታ ቤተ እስራኤል በዓለ ስርየት፣ በዓለ ሰዊትን፣ ፋሲካን፣ በዓለ ሀምሳ ወይም በዓለ ጰንጤ ቆስጤን ከያሉበት ሀገር ወደ ኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ መጥተው ለሐምሳ ቀናት የሚሰባሰቡበትና የሚሳለሙበት ሕግ ስላላቸው ሕዝቡ እንዳይታወክ ሰግተው ነበር፡፡ አንድም በሆሣዕና ዕለት በክብር ሲቀበሉት ወደቤተ መቅደስም ሲሸኙት ስላዩ እንዴት እንደሚይዙትና እንደሚገድሉት ፈርተው ተጨነቁ፡፡
የካህናት አለቆችና የሕዝብ ሹማምት በጌታችን ላይ ይሙት በቃ ለመወሰን የሰበሰቡት ሸንጐ “ሲኒሃ ድርየም” ይባላል፡፡ በዚህ ሸንጐ ላይ በአብዛኛው የተሰየሙት ሰዱቃውያን ሲኾኑ ሌሎቹ ደግሞ ጸሐፍት ፈሪሳውያን ነበሩ፡፡ ሸንጐው በአጠቃላይ ሰባ ሁለት አባላት የነበሩት ሲኾን የሚመራውም በሊቀ ካህናቱ ቀያፋ ነበር፡፡ ከዳተኛው ይሁዳም ጸሐፍት ፈሪሳውያንና የካህናት አለቆች በጌታችን ላይ የነበራቸውን ጥላቻ ያውቅ ስለነበር “ምን ልትሰጡኝ ትወዳላችሁ? እኔም አሳልፌ እሰጣችኋለሁ፤” በማለት ጌታችንን አሳልፎ ሊሰጣቸው እንደሚችል ተስማምቷል፡፡ ጌታችን በሚያስተምርበት ወቅት የአስቆሮቱ ይሁዳ ከምእመናን የሚገባውን ገንዘብ ሰብሳቢ ነበር፡፡ ከሚሰበሰበው ሙዳየ ምጽዋት ለግል ጥቅሙ እየቆረጠ የማስቀረት የእጅ አመል ነበረበት፡፡
ይህ ድብቅ አመሉ ጎልቶ የወጣው ጌታችን በለምጻሙ በስምዖን ቤት ሳለ ማርያም እንተ እፍረት ወይም ባለሽቱዋ ማርያም ዋጋው ውድ የሆነ ሽቱ በራሱ ላይ ባፈሰሰች ጊዜ ይሁዳ “ይህ ሽቱ ተሽጦ ለድሆች ቢሰጥ መልካም ነበር፤” ያለው ሽቱ ሲሸጥ የሚያገኘውን ጥቅም በማሰብ ነው፡፡ ይሁዳ ተቆርቋሪ መስሎ ያቀረበው አሳብ ተቀባይነት በማጣቱም ማኩረፊያ ያገኘ መስሎት በቀጥታ ከካህናት አለቆች ዘንድ ሔዶ ጌታችንን በሠላሳ ብር ለመሸጥ ተዋዋለ፡፡ ጌታችን ሁሉን ቻይ እንደሆነ ከዋለበት ውሎ ካደረበት አደሮ ደቀ መዝሙሩ ሆኖ ቢመለከትም፣ ቢጠይቀው ሊሰጠው በሚችለው ሠላሳ ዲናር ሸጠው፡፡ ይህም ልቡ ከዳተኛ ስለሆነ ነው፡፡ ልባቸው የታመነ ገዳማውያን ግን ሕማሙንና ሞቱን እያሰቡ ዓለምን ንቀው ይኖራሉ፡፡ ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡
ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

2 months ago