ኢራን የባቢል ማንደብን የንግድ መስመር እንደምትዘጋ ዛተች የአለም ንግድ ምን ይገጥመዋል?
የኔታ ሚዲያ
የኢራን ከፍተኛ መሪ ሞጅታባ ካሜኒ አማካሪ የኢራን ወዳጆች የሆርሙዝ ስትሬትን እንደዘጉት ሁሉ የባቢል-ማንደብን የንግድ መስመርም ሊዘጉ እንደሚችሉ አስጠነቀቁ።
ይህ እርምጃ ከተወሰደ ከዓለም የኢነርጂ አቅርቦት አንድ አራተኛው (25%) የሚሆነው ይቋረጣል ተብሎ ይፈራል።
ቀደም ሲል የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩትና በአሁኑ ወቅት የከፍተኛው መሪ አማካሪ የሆኑት አሊ አክባር ቬላያቲ እሁድ ዕለት በማህበራዊ ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት
የመቋቋም ግንባር ለባቢል-ማንደብ ያለው እይታ እንደ ሆርሙዝ ነው ብለዋል። አክለውም ዋይት ሀውስ ሞኝነት የተሞላበት ስህተት ከተደገመ የዓለም ንግድና ኢነርጂ ፍሰት በአንድ እርምጃ ሊስተጓጎል እንደሚችል አስታውቀዋል።
ይህ ማስጠንቀቂያ የመጣው የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን የሆርሙዝ ስትሬትን ለመክፈት ካልተስማማች ከፊታችን ረቡዕ ጀምሮ የሃይል ማመንጫዎቿንና ድልድዮቿን እደበድባለሁ የሚል ዛቻ ካሰሙ በኋላ ነው።
ባቢል-ማንደብ ቀይ ባህርን ከኤደን ባህረ ሰላጤ ጋር የሚያገናኝ ሲሆን በየመን እና በጅቡቲ/ኤርትራ መካከል የሚገኝ ስትራቴጂካዊ መስመር ነው።
በ2024 ብቻ በቀን 4.1 ቢሊዮን በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ በዚህ መስመር አልፏል።
ከአለም አጠቃላይ የንግድ ልውውጥ 10 በመቶው በዚህ መስመር የሚያልፍ ሲሆን በተለይም ከቻይና እና ህንድ ወደ አውሮፓ የሚላኩ ምርቶች መተላለፊያ ነው።
የሆርሙዝ ስትሬት በመዘጋቱ ምክንያት ሳውዲ አረቢያ ነዳጇን በየብስ ቧንቧ ወደ ቀይ ባህር በማምጣት በባቢል-ማንደብ በኩል ለመላክ እየተጠቀመችበት ትገኛለች።
መስመሩ በአሁኑ ወቅት በኢራን የሚደገፉት የየመን ሁቲ አማጺያን ቁጥጥር ስር እንደመሆኑ የሆርሙዝ እና የባቢል-ማንደብ መስመሮች በአንድነት ቢዘጉ የአለም የነዳጅ እና ጋዝ አቅርቦት 25 በመቶ ይቋረጣል።
ይህ መስተጓጎል በፋብሪካዎች፣ በቤት ውስጥ ኩሽናዎች እና በነዳጅ ማደያዎች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪና የኢኮኖሚ ውጥንቅጥ ያስከትላል።
ከእስያ ወደ አውሮፓ የሚላኩ የንግድ ኮንቴይነሮች አማራጭ ረጅም መንገድ እንዲጓዙ ስለሚያስገድድ የሸቀጦች ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ይናራል።
ኢራን የሆርሙዝ ስትሬት ክፍት የሚሆነው ከእሷ ጋር ለሚደራደሩ ሀገራት ብቻ እንደሆነ ስትገልጽ አሜሪካ እና እስራኤል ግን በዚህ እድል እንደማይጠቀሙ አስታውቃለች ይህም ቀጠናውን ወደ ከፋ ወታደራዊ ግጭት ሊከተው ይችላል የሚል ስጋት አንግሷል።

2 months ago