Logo
YenetaTube
የትራምፕ የግል ስድብ እና የማክሮን ምላሽ፦ የፈረንሳይ እና የአሜሪካ ዲፕሎማሲያዊ ፍጥጫ
የኔታ ሚዲያ

የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት አማኑኤል ማክሮን የአሜሪካ አቻቸው ዶናልድ ትራምፕ በትዳራቸው ላይ ለሰነዘሩት መሳለቂያ ጥብቅ ምላሽ ሰጡ።

ትራምፕ ፈረንሳይ በአሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ ለጀመሩት ወታደራዊ ዘመቻ ድጋፍ አልሰጥም ማለቷን ተከትሎ ነው ይህንን የግል ትችት የሰነዘሩት።

ባለፈው ረቡዕ በዝግ ዝግጅት ላይ የተገኙት ትራምፕ ማክሮን በመካከለኛው ምስራቅ ጉዳይ አሜሪካን አልረዳም ማለታቸውን በመንቀፍ "ፈረንሳይን ደውዬ ነበር ባለቤቱ በጣም የምታሰቃየው ማክሮን አሁንም በመንጋጋው ላይ ካረፈበት ምት እያገገመ ነው" ሲሉ ተሳልቀዋል።

ይህም እ.ኤ.አ. በ2025 ባለቤታቸው ብሪጅት ማክሮን በፕሬዝዳንታዊ ጄት ውስጥ ፊታቸውን ሲገፉ የታዩበትን ተንቀሳቃሽ ምስል ላይ አስተያየት የሰጡት

በደቡብ ኮሪያ ይፋዊ ጉብኝት ላይ የሚገኙት ማክሮን ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ የትራምፕ ንግግር ጨዋነት የጎደለው እና ደረጃውን ያልጠበቀ ነው ብለዋል።

ፈረንሳይ በኢራን የኒውክሌር መሰረተ ልማት ላይ ለሚሰነዘር ጥቃት በቀጥታ ወታደራዊ ድጋፍ ከመስጠት ተቆጥባለች።
ፈረንሳይ፣ ስፔን እና ጣሊያን የአሜሪካ የቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች የአየር ክልላቸውን እንዳይጠቀሙ ከልክለዋል።

ማክሮን የአሜሪካን የባህር ኃይል ዘመቻ ለመደገፍ ፈቃደኛ ባይሆኑም፣ ውጥረቱ ከረገበ በኋላ ጥበቃ ለማድረግ ቃል ገብተዋል። ይህም በዋይት ሃውስ ዘንድ መሳለቂያ ሆኖባቸዋል።

የትራምፕ ንግግር በፈረንሳይ ፖለቲከኞች ዘንድ ከፍተኛ ተቃውሞ አስነስቷል። የፈረንሳይ ብሔራዊ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ያኤል ብራውን ፒቬት እንዲህ ብለዋል፦
ስለ አለም ቀጣይ እጣ ፈንታ እየተወያየን ባለበት እና ሰዎች በጦር ሜዳ እየሞቱ ባሉበት ወቅት ሌሎችን የሚያሾፍ እና የሚሳለቅ ፕሬዝዳንት ማየታችን ተገቢ አይደለም ሲሉ ተደምጠዋል

የግራ ዘመም መሪው ማኑኤል ቦምፓርድም የትራምፕን ንግግር "በፍጹም ተቀባይነት የሌለው" ሲሉ አውግዘዋል።

ትራምፕ ከዚህ ቀደም የማክሮንን የግል መልዕክቶች ይፋ በማድረግ እና የፈረንሳይኛ ዘይቤያቸውን በመምሰል ሲቀልዱባቸው እንደነበር ይታወሳል።

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.