የኢትዮጵያ ተማሪዎች ምገባ ኢኒሼቲቭ በደቡብ ሱዳን ፕሮግራሙን ለመጀመር ተፈራረሙ!
#fastmereja I በኢትዮጵያ የተማሪዎች ምገባ ኢኒሼቲቭ (ESMI) በምስራቅ አፍሪካ ቀጠና የሰው ሀብት ልማት ላይ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት የመግባቢያ ስምምነት ከሰንራይዝ ፋውንዴሽን (Sunrays Foundation) ጋር በዛሬው ዕለት አከናዉኗል።
ይህ ስምምነት በደቡብ ሱዳን ሪፐብሊክ የተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም በይፋ ለመጀመር የሚያስችል ስምምነት መሆኑ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ የትምህርት ቤቶች ምገባ ኢኒሼቲቭ ዳይሬክተር ወ/ሮ ፍሬአለም ሽባባዉ እንደገለፁ፣ባለፉት ዓመታት ድርጅቱ በኢትዮጵያ የዘረጋው ዘላቂ የምገባ ሞዴል ውጤታማ መሆኑን ተከትሎ፣ በቀጠናው ሀገራት ዘንድ ተቀባይነትን በማግኘቱ አሁን ላይ የምስራቅ አፍሪካ ቢሮውን በማቋቋም ተደራሽነቱን እያሰፋ እንደሚገኝም ገልፀዋል።
በዛሬው ዕለት ከሰንራይዝ ፋውንዴሽን ጋር የተፈረመው ስምምነት፣ የኢትዮጵያ የተማሪዎች ምገባ ኢኒሼቲቭ በደቡብ ሱዳን ሪፐብሊክ በምዕራብ ኢኳቶሪያ ግዛት ስር በምትገኘው ያምቢዮ (Yambio) ከተማ የምገባ ፕሮግራሙን ወዲያውኑ ለመጀመር የሚያስችል ስለመሆኑም ተነግሯል።
ይህ ፕሮጀክት በደቡብ ሱዳን የሚገኙ ህፃናትን የምግብ ዋስትና ከማረጋገጡ ባለፈ፣ ተማሪዎች በትምህርታቸው ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ ትልቅ እገዛ እንደሚያደርግ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ የተማሪዎች ምገባ ኢኒሼቲቭ ልዩ መለያ ከተለመደው የጥሬ ምግብ እርዳታ ባለፈ፣ በአካባቢ ምርት ላይ የተመሰረተና በመንግስት የሚደገፍ ስነ-ምህዳርን መገንባት ላይ ያተኮረ መሆኑ ነው፡፡
ይህ አሰራር የአካባቢው አርሶ አደሮች ምርታቸውን ለትምህርት ቤቶች እንዲያቀርቡ ዕድል ይፈጥራል፤ በመንግስትና በግል ዘርፍ መካከል ጠንካራ ትብብር እንዲኖር የሚያደርግ እንዲሁም የቀጠናውን የሰው ሀብት ልማት በዘላቂነት ለማሳደግ መሰረት የሚጥል መሆኑ ተጠቅሷል።
ይህ ታሪካዊ ስምምነት ኢትዮጵያ በተማሪዎች ምገባ ዘርፍ ያካበተችውን ልምድ ለጎረቤት ሀገራት የምታጋራበትና ቀጠናዊ ትስስርን በልማት የምታጠናክርበት ትልቅ ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል።
የኢትዮጵያ የተማሪዎች ምገባ ኢኒሼቲቭ (ESMI) እ.ኤ.አ. በ2013 የተመሰረተ ሲሆን፣ መነሻውም አንድ ተማሪ ባዶ የምሳ ዕቃውን በትምህርት ቤት ውስጥ ደብቆ በነበረበት ወቅት በተስተዋለ እውነታ ላይ የተመሰረተ መሆኑ ነዉ የተገለፀዉ።
ይህ አጋጣሚ የተማሪዎች ምገባን ከሰብዓዊ እርዳታ ባለፈ፣ ሀገራዊና ስልታዊ ቅድሚያ የሚሰጠው የልማት ተግባር ለማድረግ የሚያስችል ራዕይ እንዲወለድ ምክንያት ሆኗል።

6 months ago