የአሳ ምርት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 95 በመቶ ብልጫ ማሳየቱ ተገለፀ
በበጀት ዓመቱ ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ከንጋት ሐይቅ 7ሺህ 932 ቶን የዓሣ ምርት ተመርቷል፤ ይህ የዓሣ ምርት መጠን ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ95 በመቶ ብልጫ ማሳየቱን የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ግብርና ቢሮ የዓሳ ኃብት ልማት ባለሙያ አቶ ቡሸን ፉፋ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ 9 ሺህ 665 ቶን ዓሣ ለማምረት ታቅዶ ወደ ሥራ የተገባ ሲሆን እስካሁን 7ሺህ 932 ቶን የዓሳ ምርት ተመርቷል። የዓሣ ምርት በብዛት የሚገኘው በሁለተኛው መንፈቀ-ዓመት ስለሆነ ዕቅዱን ማሳካት የሚያስቸሉ ሁኔታዎች መፈጠራቸው ተገልጿል።
ቀደም ሲል በተካሄደ ጥናት ውጤት መሠረት በታላቁ ህዳሴ ግድብ በንጋት ሐይቅ 29 የዓሣ ዝርያዎች ያሉ ሲሆን፤ አሁን በብዛት ለገበያ እየቀረቡ ያሉት ሦስት ዓይነት ዝርያዎች ለማዕከላዊ ገበያ እየቀረበ ሲሆን በተዘረጋው የገበያ ትሥሥር መሠረት በአግባቡ ምርት ለገበያ እየቀረበ ይገኛል።
በዓሣ ማሥገር ዘርፍ 80 ማኅበራት የተደራጁ ሲሆን ከእነዚህ መካከል 35 ማኅበራት ወደ ሥራ ገብተው እያመረቱ ይገኛሉ።ከንጋት ሐይቅ እየተመረተ ያለው የዓሣ ምርት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ሲሆን ለአብነትም በ2017 ደግሞ 5 ሺህ 993 ቶን ዓሣ ምርት መመረቱ ይታወሳል።
seledadotio

2 months ago