በኮተቤ መስመር 02 አካባቢ ከባድ የትራፊክ አደጋ ተከሰተ
በአዲስ አበባ ከተማ ኮተቤ 02 መስመር በተለምዶ አንቆርጫ ተብሎ በሚጠራው ቁልቀለት መንገድ ከተፈቀደለት ጭነት በላይ 19 ሰዎችን ይዞ ፣ ሲጓዝ የነበረ የህዘብ ማመላለሻ / ታክሲ// ከንጋቱ 11፡30 አካባቢ ከፍተኛ የትራፊክ አደጋ ደርሶበታል።
በአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን የየካ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስራ አስኪያ አቶ ተክሌ ካሳዬ እንደገለጹት አደጋው የደረሰው በየረር አቅጣጫ አንቆርጫ መስመር ቁልቁለቱን ሲጓዝ የነበረ ይኸው ታክሲ የመንገድ አካፋይን ጥሶ የመጋጨትና የመገልበጥ አደጋ ደርሶበታል፡፡
የጽጽቤቱን ባለሙያዎች በመያዝ በሰዓቱ ስፍራው ተገኝተው እና ከአይን እማኞች እንደተረዱት ታክሲው ከተፈቀደለት ጭነት በላይ ተሳፋሪዎችን እንደያዘና የትራፊክ አደጋ እንደደረሰበት እና በተሳፋሪዎችም ላይ ከባድ ጉዳት እንዳጋጥሟል፡
አቶ ተክሌ አያይዘውም የአደጋው መንስኤ በትራፊክ ፖሊስ እንደሚጣራ እና አሽከርካሪዎች ግን ተሳፋሪዎችን ከተፈቀደላቸው ቁጥር በላይ ባለመጫን አደጋን ቀድመው አንዲከላከሉ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

3 months ago