የአርቲስት ጥላዬ ጨዋቃ ሥራዎቹ
#ethiopia | በአዳማ (ናዝሬት ) ሳር ሰፈር በሚባለው አካባቢ በ1947 ዓ .ም ነው የተወለዱት ።
የአንደኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአጼ ገላውዲወስ ት/ቤት ተከታትለዋል ።
ለሙዚቃ በነበረው ዝንባሌ እና ፍቅር የምድር ጦር ሙዚቃ ክፍልን ሰኔ 2 ቀን 1961 ዓ.ም በኮለኔል ለማ ደምሰው እና ሻምበል ታደሰ ተክሉ ተፈትነው ምድር ጦር ኦርኬስትራን ተቀላቅለው ለ22 አመታት አገልግለዋል።
1983ዓም ላይ ኢህአዴግ አዲስ አበባን ሲቆጣጠር ኦርኬስትራው ፈረሰ። ቶሎሳ ቆቱ ሰፈር ረጅም አመታት የኖሩት አርቲስት ጥላዬ ጨዋቃ ከእድሩ መጽሔት ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለፁት የደረሰባቸውን በደል ተናግረዋል ።
ያለምንም ደም፣ ጀግናው ወታደር፣ ጠንካራው መምህር፣ ዘማች አሸወይና፣ ኮረሪማ፣ ንቦዬ ከሥራዎቹ ጥቂቶቹ ናቸው።
አርቲስት ጥላዬ ጨዋቃ በድምፃዊነቱ ብቻ ሳይሆን በግጥም እና ዜማ ደራሲነቱም የሚታወቅ፣ በተለይም በምድር ጦር ኦርኬስትራ ውስጥ ለረጅም ዓመታት ያገለገለ አንጋፋ የጥበብ ሰው ነው።
የአርቲስት ጥላዬ ጨዋቃ የማይረሱ የሙዚቃ ስራዎች
"ታታሪው ሹፌር"
ጠመዝማዛው መንገድ ኮረብታው
ሽቅብ ቁልቁለት
በረሃ አቋራጭ ጋላቢ ዳገት
የሹፌሮችን የህይወት ውጣ ውረድ እና በረሃ አቋራጭ ጉዟቸውን በሚገርም ሁኔታ የገለጸበት፣ እስከ ዛሬ ድረስ በታክሲም ሆነ በረጅም መንገድ አሽከርካሪዎች ዘንድ እንደ መዝሙር የሚቆጠር ስራው ነው።
"ያለምንም ደም"
ወቅታዊ ኩነቶችን በሙዚቃው ለመግለጽ የነበረውን ጥበብ የሚያሳይ ነው።
"ዘማች አሸወይና"
በምድር ጦር ኦርኬስትራ ውስጥ በነበረበት ወቅት ካከናወናቸው ጉልህ ስራዎች አንዱ።
"ኮረሪማ"
ለቅጥር ፈተና የተጠቀመበትና ድምፁን በሚገባ ያስመሰከረበት ስራው።
"ንቦዬ"
በብዙዎች ዘንድ የምትታወቅና የምትወደድ ዜማው።
"ጠንካራው መምህር"
ለሙያተኞች ያለውን አክብሮት በዜማ የገለጸበት።
ለጥበብ የነበረው ጽናት
የአርቲስቱ የህይወት ታሪክ እንደሚያሳየው፣ ከኦርኬስትራ መፍረስ በኋላ የገጠመውን ፈተና በጽናት ማለፉ ለብዙዎች ትምህርት የሚሰጥ ነው። "ስራን ካወከው ማንነትን... የሚያስረዳ ነው" በማለት እንጀራ በመሸጥም ቢሆን ቤተሰቡን ደግፎ እዚህ መድረሱ፣ ከጥበብ ሰውነቱ ባሻገር ጠንካራ የቤተሰብ መሪ እንደነበረ ያሳያል።
የ71 ዓመት የህይወት ጉዞውን አጠናቆ ቢያልፍም፣ ስራዎቹ ግን ለትውልድ ሲዘከሩ ይኖራሉ።
ድምጻዊና ደራሲ ጥላዬ ጨዋቃ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በ71 ዓመታቸው አርብ መጋቢት 18/2018 ዓ .ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
* "...እንግዲህ እኔ አዲስ አበባ የመጣሁት በ1961 ዓ/ም ሰኔ 1 ነው ። እንዳጋጣሚ ሰኔ 1 እሁድ ቀን ዋለ፣ እኔ ሰኔ 2 ቀን ምድር ጦር ለፈተና ገባሁ ፈተናው አሁን እንደሚሰጠው አጥንተህ አይደለም። 'እስኪ ይሔንን ዝፈን!' ነው የምትባለው። ስትዘፍን ካንተ የሚወስዱት ነገር አለ። ትንፋሽህን፣ ድፍረትህን፣ ስትጫወት ፊትህ ላይ የሚነበበውን ነገር ይወስዳሉ። 'ይሔ ለመድረክ ተገቢ ነው ፣ወደፊትም የኛ አባል ሊሆን ይችላል' የሚል ነገር ይወስዳሉ ። አጋጣሚ ስፈተን ከፊቴም፣ ከኋላዬም ማንም አልነበረም ብቻዬን ነው የተፈተንኩት ። ፈተናውን የፈተኑኝ ኮለኔል ለማ ደማስ እና ሻምበል ታደሰ ተክሉ ይባላሉ። በወቅቱ ምክትል አዛዥ ነበሩ። እናም 'ኮረሪማ' በሚለው ዘፈን ተፈተንኩ ፈተናውን በጥሩ ሁኔታ አለፍኩ ተቀጠርኩ። እናም አይረሴ የሆኑና ማህበራዊ ፋዬዳ ያላቸውን ስራዎችን ሰርቻለሁ።"
* "... አፄ ገላውዲዮስ ት/ቤት ናዝሬት ወይንም አዳማ እዛ ነው ሙዚቃን የጀመርኩት። የት/ቤት እንቅስቃሴ ውስጥ የሙዚቃ ክበብ አቋቁመን ከአንጋፋዎቹ ጋር መድረክ ላይ አንዳንድ ቲያትሮችን እና ሙዚቃ እንሰራ ነበር ። እኔ በሙዚቃ ክፍል ነበርኩ።... ማንም ሳያሳየን እንዲህ በሉ ሳይለን፣ ደራሲ በሌለበት ቦታ ከጓደኞቼ ጋር አዳዲስ ስራዎችን እየደረስን፣ ያዳመጥነውን የሰዎች ኮሌኬሽን እሱንም እየሰራን አደግን።"
* "...የጠፋሁት የውዴታ ግዴታ ሆኖብኝ ነው። ኢህአዴግ ኢትዮጵያን ሲቆጣጠር በጦር ሜዳሜ ያለውም የምድር ጦር የሙዚቃ ቡድንም ባጠቃላይ ካምፕ ውስጥ የተቀመጠው ጭምር ደሞዝ ተከልክለን ተበተንን። ብዙ ቤተሰብ ይዘናል የግድ ሆነና ተበተንን። እኔና የሙያ ባልደረቦቼም ከምንወደው ሙያችን እራቅን።"
* "... በተለያዩ ኤምባሲዎች ጋር እሰራ ነበር። ጥሩ የእንግሊዝኛ ችሎታ ያለው ሰው ፈልገው ተቀጥሬ ሰርቻለሁ። በዓለም ላይ የሚጠላ ስራ የለም ስራን ካወከው ማንነትን፣ ሰው መሆንህን የሚያስረዳ ነው። እናም ያኔ እንዲህ ያማረ ቤት ውስጥ አልነበረም የምንኖረው። ለመግለፅ የሚከብድ ቤት ነበረች። የባለቤቴ ዘመድ ስታየን በጣም አዘነች እናም 'እኔ አንድ ነገር ላድርግላችሁ፣ መንቀሳቀሻዬ ስለሆነ ትመልሳላችሁ። ለመመለስ ግን ትንሽ ግዜ መጎዳት ይኖርባችኋል ። እስከዚያው የድሮ ስራችሁን ትሰራላችሁ!' አለችን። የድሮ ስራ ያለችን ሚስቴ እንጀራ ትጋግራለች እኔ ቤት በምውል ግዜ ደግሞ እንጀራ እሸጣለሁ ብቻ በመተጋገዝ ከፈጣሪ ጋር እዚህ ደረጃ ላይ ደርሰናል ።"
ድምጻዊ የግጥም እና የዜማ ደራሲ ጥላዬ ጨዋቃ በናዝሬት (አዳማ) ሳር ሰፈር ነበር የተወለደው።
የድምጻዊ ጥላዬ ጨዋቃን ስራ የምታስታውሱ ጠቆም አድርጉ። እኔ ልጀምር 'ጠምዝማዛው መንገድ..' ...ቀጥሉ።
ድምጻዊና ደራሲ ጥላዬ ጨዋቃ ባለ ትዳር እና የ3 ሴት ልጆች አባት ነበሩ።
መጋቢት 19 ቀን 2018 ዓ.ም በቤተል ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ቀብሩ ተፈጽሟል።
ለመላ ቤተሰቦቻቸው መጽናናቱን ይስጥልን ።

6 months ago