አዲስ አበባ በ170 ሚ. ብር ግዙፍ
"የኤሌክትሪክ ኃይል ማደያ" ባለቤት ሆነች
#ethiopia | የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በአዲስ አበባ ኮተቤ አካባቢ በአንድ ጊዜ 24 ተሽከርካሪዎችን ማስተናገድ የሚችል ዘመናዊ የኃይል መሙያ ጣቢያ ዛሬ በይፋ አስመርቋል።
በ170 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባው ይህ ጣቢያ በቀን 24 ሰዓት አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን፣ በተለይም የኃይል ጭነት በማይኖርበት ወቅት ደንበኞች ተሽከርካሪዎቻቸውን እንዲሞሉ ለማበረታታት "ምክንያታዊ" የዋጋ ተመን ተፈጻሚ ተደርጓል።
በተጨማሪም በፒያሳ ኤሌክትሪክ ሕንፃ ግቢ ውስጥ የተገነባ ሌላ የኃይል መሙያ ጣቢያም ዛሬውኑ ሥራ መጀመሩ ታውቋል።
በትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር በኩል እንደተገለጸው፣ በአሁኑ ወቅት ከ140 ሺህ በላይ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ሲሆን፣ ሀገሪቱ ለነዳጅ ግዢ የምታወጣውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ለመቀነስ አረንጓዴ ኢኮኖሚን በቁርጠኝነት እያሳደገች ትገኛለች።
ይህ የኃይል መሙያ ጣቢያ መመረቅም በመንገድ ላይ ለሚቆሙ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ባለቤቶች ትልቅ እፎይታን የሚሰጥና በዘርፉ ለሚሰማሩ የግል ባለሀብቶችም መንግሥት ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል።
ተቋሙ በመጀመሪያው ምዕራፍ በአዲስ አበባ 32፣ በሌሎች የሀገሪቱ ከተሞች ደግሞ 8 በድምሩ 40 የኃይል መሙያ ጣቢያዎችን ለመገንባት በከፍተኛ ትኩረት እየሠራ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ጌቱ ገረመው አስታውቀዋል።
ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት ኢትዮጵያ በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች አጠቃቀም ረገድ በአጭር ጊዜ ውስጥ ያስመዘገበችውን ውጤት ይበልጥ የሚያጠናክርና ለወደፊትም የትራንስፖርት ዘርፉን ወደ ኤሌክትሪክ ለመቀየር ለተያዘው ግብ ትልቅ መሠረት የሚጥል ነው።

3 months ago