ከኢራን ጋር ግንኙነት ያላቸው ጠላፊዎች (Hackers) የኤፍ ቢ አይ (FBI) ዳይሬክተር የሆኑትን ካሽ ፓቴል የግል ኢሜል፣ ፎቶግራፎች እና ሰነዶች መዝረፋቸውን ይፋ አደረጉ።
የኔታ ሚዲያ
ባለፈው አርብ የጠላፊ ቡድኑ እና ቢሮው እንዳስታወቁት ከኢራን ጋር ንክኪ ያላቸው ጠላፊዎች የኤፍ ቢ አይ ዳይሬክተር ካሽ ፓቴልን የግል የኢሜል ሳጥን በመስበር ፎቶግራፎቻቸውን እና ሌሎች ሰነዶችን በኢንተርኔት ላይ በትነዋል።
''ሃንዳላ ሃክ ቲም" (Handala Hack Team) የተባለው የጠላፊ ቡድን በድረ-ገጹ ላይ ባሰፈረው መረጃ ፓቴል አሁን በስኬት ከተጠለፉ ሰለባዎች ዝርዝር ውስጥ ስሙን ያገኘዋል ብሏል።
ጠላፊዎቹ ፓቴል ሲጋራ ሲያጨስ በጥንታዊ ተሽከርካሪ ውስጥ ሲጓዝ እና ትልቅ የረም (rum) ጠርሙስ ይዞ በመስተዋት ፊት ፎቶ ሲነሳ የሚያሳዩ ተከታታይ የግል ምስሎችን አሰራጭተዋል።
ኤፍ ቢ አይ የፓቴል ኢሜሎች ኢላማ መደረጋቸውን አረጋግጧል። የኤፍ ቢ አይ ቃል አቀባይ ቤን ዊሊያምሰን በሰጡት መግለጫ ከዚህ ድርጊት ጋር ተያይዘው ሊመጡ የሚችሉ አደጋዎችን ለመቀነስ አስፈላጊ የሆኑ እርምጃዎችን ሁሉ ወስደናል ብለዋል።
በተጨማሪም የተዘረፉት መረጃዎች የቆዩ እና ምንም አይነት የመንግስት መረጃ የሌለባቸው መሆናቸውን ገልጸዋል።
ራሱን የፍልስጤም ደጋፊ አድርጎ የሚያስተዋውቀው ሃንዳላ በምዕራባውያን ተመራማሪዎች ዘንድ የኢራን መንግስት የሳይበር ደህንነት ክፍሎች ከሚጠቀሙባቸው መጠሪያዎች አንዱ እንደሆነ ይታመናል።
ቡድኑ በቅርቡ መጋቢት 2 ቀን በሚቺጋን የሚገኘውን ስትራይከር (Stryker) የተባለ የህክምና መሳሪያዎች አቅራቢ ድርጅትን መጥለፉንና በርካታ የኩባንያውን መረጃዎች ማጥፋቱን ገልጾ ነበር።
ከፎቶግራፎቹ በተጨማሪ ጠላፊዎቹ ከ300 በላይ የኢሜል ናሙናዎችን ያሰራጩ ሲሆን እነዚህም ከ2010 እስከ 2019 ባሉት ዓመታት ውስጥ የተላላኩ የግል እና የስራ ግንኙነቶችን የሚያሳዩ ይመስላሉ።
የሮይተርስ የዜና ምንጭ መልእክቶቹን በራሱ ማረጋገጥ ባይችልም ሃንዳላ ሰብሬዋለሁ የሚለው የጂሜል (Gmail) አድራሻ ከዚህ ቀደም በ ዲስክትሪክት 4 ላብስ የደህንነት ተቋም በተመዘገቡ መረጃዎች ላይ ከፓቴል ጋር የተያያዘ መሆኑ ተረጋግጧል።
ባለፈው ወር አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ የተቀናጀ ጥቃት ካደረሱ በኋላ ድምፃቸውን አጥፍተው የነበሩት ከኢራን ጋር ግንኙነት ያላቸው ጠላፊዎች አሁን ላይ የሳይበር ጥቃቶቻቸውን በስፋት እያወደሱ ይገኛሉ።
ከፓቴል ጥቃት በተጨማሪ ቡድኑ በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ የሎክሂድ ማርቲን የመከላከያ ኩባንያ ሰራተኞችን የግል መረጃ መዝረፉን ገልጿል።
የእስራኤሉ ቼክ ፖይንት የሳይበር ደህንነት ኩባንያ የስራ ሃላፊ ጊል ሜሲንግ እንደገለጹት በፓቴል ላይ የተሰነዘረው ጥቃት የአሜሪካ ባለስልጣናትን ለማሳፈር እና ተጋላጭ እንደሆኑ እንዲሰማቸው ለማድረግ ያለመ የኢራን ስትራቴጂ አካል ነው።
ኢራናውያን ያላቸውን ሁሉንም መሳሪያ እየተኮሱ ነው ያሉት ሜሲንግ የከፍተኛ ባለስልጣናትን የግል ኢሜል መጥለፍ አዲስ ነገር እንዳልሆነና አልፎ አልፎ የሚከሰት መሆኑን አስረድተዋል።
በመጋቢት 2 የወጣ የአሜሪካ የስለላ ግምገማ እንደሚያመለክተው ኢራን እና ተላላኪዎቿ ለከፍተኛ መሪዎቿ መገደል ምላሽ ለመስጠት በአሜሪካ የዲጂታል መረቦች ላይ መሰል የሳይበር ጥቃቶችን ሊሰነዝሩ እንደሚችሉ ተገምቶ ነበር።

3 months ago