ጊፍት ሪል እስቴት ለፋሲካ በዓል የ15% የአፓርትመንትና የንግድ ቤቶች ሽያጭ ቅናሽ አቀረበ
#fastmereja I አዲስ አበባ
ጊፍት ሪል እስቴት የፋሲካን በዓል ምክንያት በማድረግ በመላው አገሪቱ ለሚገኙ ደንበኞቹ የአፓርትመንትና የንግድ ቤቶች ሽያጭ ላይ የ15% ቅናሽ ማድረጉን በዛሬው ዕለት ለገሃር በሚገኘው የግንባታ ስፍራ በተከናወነ ፕሮግራ ላይ ተነግሯል። ድርጅቱ በዓሉን አስመልክቶ ባዘጋጀው ልዩ ሽያጭ ደንበኞች በ2% ቅድመ ክፍያ ብቻ የቤት ባለቤት መሆን የሚችሉበትን ዕድል አመቻችቷል።
ይህ ልዩ የሽያጭ ማበረታቻ እስከ ሚያዝያ 19 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ለአንድ ወር የሚቆይ ይሆናል። በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ 1,200 ቤቶች ለገበያ የቀረቡ ሲሆን፣ ይህም በዝቅተኛ ቅድመ ክፍያ የቤት ባለቤት ለመሆን ለሚፈልጉ ዜጎች ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥር ተገልጿል።
ኩባንያው በአሁኑ ወቅት በሰሚት አካባቢ በ4 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ከ4 ሺህ በላይ ቤቶችን ያካተተ "የጊፍት ሜትሮፖሊታን መንደር" ግንባታ እያከናወነ ይገኛል። በአጠቃላይ በለቡ፣ በ22 ማዞሪያ፣ በሲኤምሲ እና በቦሌ መድኃኒዓለም አካባቢዎች ከ16 ሺህ በላይ የመኖሪያና የንግድ ቤቶችን ለህብረተሰቡ እያቀረበ መሆኑ ተነግሯል። እነዚህ መንደሮች ዘመናዊ የትምህርት ቤቶች፣ የህክምና ተቋማት እና የመዝናኛ ስፍራዎችን ያካተቱ እንደሆኑ ተገልጿል።
መጋቢት 19 ቀን 2018 ዓ.ም

3 months ago