#ሰበር_ዜና
የአሜሪካ እጅግ ዘመናዊ የጦር መሣሪያዎች በኢራን ሚሳይሎች እየወደሙ ነው!
ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በአሜሪካና በኢራን መካከል የተቀሰቀሰው ጦርነት ለአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር እጅግ አስደንጋጭ የገንዘብና የቁሳቁስ ኪሳራ እያስከተለ መሆኑ ተሰማ።
የዎል ስትሪት ጆርናል ባወጣው አዲስ መረጃ መሠረት፣ ጦርነቱ በተጀመረ በመጀመሪያዎቹ ሦስት ሳምንታት ውስጥ ብቻ አሜሪካ ከ1.4 ቢሊዮን እስከ 2.9 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት የጦር መሣሪያ ኪሳራ ደርሶባታል።
ይህ ከፍተኛ ውድመት የተመዘገበው ኢራን በወሰደችው መጠነ ሰፊ የሚሳይልና የድሮን ጥቃት መሆኑን የቀድሞ የፔንታገን ከፍተኛ ባለሥልጣን ኢሌን ማክከስከር አረጋግጠዋል።
በአየር ላይ በተሰነዘሩ ጥቃቶችና ባልተጠበቁ አደጋዎች ምክንያት የአሜሪካ አየር ኃይል ክፉኛ ተመትቷል። በመጋቢት ወር መጀመሪያ ላይ ሦስት F-15E ተዋጊ ጄቶች በኩዌት አውሮፕላን በስህተት ተመትተው የወደቁ ሲሆን፣ በአይነቱ ልዩ የሆነው F-35 የድብቅ ተዋጊ ጄትም በደረሰበት ጥቃት ምክንያት በአስቸኳይ እንዲያርፍ ተገዷል።
በተጨማሪም በሳዑዲ ዓረቢያ በሚገኘው የጦር ሰፈር ላይ ኢራን በሰነዘረችው የሚሳይል ጥቃት አምስት ግዙፍ የነዳጅ ጫኝ አውሮፕላኖች ጉዳት ደርሶባቸው ለጥገና ተዳርገዋል። ከአሥር በላይ የሚሆኑትና እጅግ ውድ የሆኑት MQ-9 Reaper ድሮኖችም በተመሳሳይ መልኩ መውደማቸው የፔንታገንን የጦር ዝግጁነት ጥያቄ ውስጥ ከቶታል።
የባሕር ኃይሉም ቢሆን ከዚህ ጥቃት አላመለከተም። በዓለም ላይ እጅግ ዘመናዊ የተባለው አውሮፕላን ተሸካሚ መርከብ USS Gerald R. Ford በመጋቢት 12 ቀን በደረሰበት የእሳት አደጋ ምክንያት በአሁኑ ወቅት በግሪክ የባሕር ወደብ ጥገና እየተደረገለት ይገኛል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ፔንታገን የወደሙበትን ቁሳቁሶች ለመተካት የ200 ቢሊዮን ዶላር ተጨማሪ በጀት ለመጠየቅ ዝግጅቱን ማጠናቀቁ ታውቋል።
ውጥረቱ የጀመረው በየካቲት ወር መጨረሻ አሜሪካና እስራኤል በጋራ በመሆን በኢራን ላይ ጥቃት መክፈታቸውን ተከትሎ ሲሆን፣ ኢራንም በሳዑዲ ዓረቢያ፣ ኳታር እና ዮርዳኖስ በሚገኙ የአሜሪካ የጦር ሰፈሮች ላይ የአጸፋ እርምጃዋን አጠናክራ ቀጥላለች።
እስካሁን በነበረው ግጭት 13 የአሜሪካ ወታደሮች መገደላቸውና 290 የሚሆኑት መቁሰላቸው ተረጋግጧል። በኢራን በኩል ደግሞ ከ1,340 በላይ ሰዎች መሞታቸው የተዘገበ ሲሆን፣ ቀጣናው አሁንም በከፍተኛ ስጋት ውስጥ ይገኛል።
seledadotio

3 months ago