Logo
YenetaTube
ኢራን በሆርሙዝ በኩል ሊያልፉ የነበሩ ሦስት መርከቦችን መመለሷን አሳወቀች

የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ዛሬ ጠዋት በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል ሊያልፉ የነበሩ ሦስት የጭነት መርከቦችን ማስመለሱን አስታወቀ።
"የተለያዩ አገራት ንብረት የሆኑ ኮንቴይነር የጫኑ ሦስት መርከቦች፤ እንዲያልፉ የተፈቀደላቸው መርከቦች በሚጓዙበት የተለየ መስመር በኩል ለማለፍ ሞክረው ነበር። የአብዮታዊ ዘቡ ባሕር ኃይል ማስጠንቀቂያ ከሰጣቸው በኋላ ወደ መጡበት ተመልሰዋል” ይላል የወጣው መግለጫ።

የአብዮታዊ ዘቡ መግለጫ ጨምሮም "የሆርሙዝ ወሽመጥ የተዘጋ በመሆኑ የትኛውም ለማለፍ የሚሞክር መርከብ ጠንካራ ምላሽ ይጠብቀዋል” ብሏል።
“የአሜሪካ እና የእስራኤል አጋሮች እና ደጋፊዎች ከሆኑ አገራት ወደቦች የሚነሱ እና ወደዚያ የሚያመራ የትኛውም ዓይነት መርከብ በሆርሙዝ በኩል እንዳያልፍ ተከልክሏል” ብሏል መግለጫው።

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ለአገሪቱ ቴሌቪዥን “ከቻይና፣ ከሩሲያ፣ ከፓኪስታን፣ ከኢራቅ እና ከሕንድ” መርከቦቻቸው በሆርሙዝ በኩል እንዲያልፉ ጥያቄ እንደቀረበላቸው ተናግረዋል።
ጨምረውም በኢራን ዕይታ ሆርሙዝ “ሙሉ ለሙሉ አልተዘጋም ነገር ግን ለጠላቶቻችን ዝግ ነው” ብለዋል።

BBC

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.