⚡️ 613 የጸጥታ አካላትና ኃላፊዎችን ጨምሮ በነዳጅ አሻጥር የተሳተፉ ግለሰቦች ታሰሩ!
#ethiopia | የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ዶ/ር ካሳሁን ጎፌ እንዳስታወቁት፤ በነዳጅ ሕገ-ወጥ ንግድ እና አሻጥር ላይ ተሳትፈው የተገኙ 613 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል።
በእስር እርምጃው ከተያዙት ግለሰቦች መካከል የንግድ ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎች፣ የቡድን መሪዎች፣ የሬጉላቶሪ ባለሙያዎች፣ የነዳጅ ማደያ ባለቤቶችና ሠራተኞች፣ እንዲሁም በየደረጃው የሚገኙ የጸጥታ አካላት ይገኙበታል።
በስድስት ክልሎች እና በሁለት የከተማ አስተዳደሮች በተደረገው ጥብቅ ፍተሻ፤ 250,221 ሊትር ቤንዚን እና 198,432 ሊትር ናፍጣ በሕገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር እና ጥቅም ላይ ሲውል ተይዞ መወረሱንም ሚኒስትሩ አብራርተዋል።
በተጨማሪም ከተወረሰው ነዳጅ ውስጥ በሽያጭ እንዲውል ከተደረገው 48,663,432.21 ብር ለመንግስት ገቢ መደረጉ ተገልጿል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ethiopia #ethiopiannews #dailynews #fuel #ministryoftrade #addisababa #ኢትዮጵያ #ዜና #ነዳጅ #አቤልብርሃኑ

7 months ago