Logo
FIDEL POST NEWS
የሞተ አንጎል የተደበቀ ግድያን እንዴት ደረሰበት ? የ12 ዓመታት አስፈሪ ምስጢር የአስክሬን ምርመራ አመለካከትን ቀየረ

​በእንግሊዝ በተፈጥሮ ምክንያት እንደሞተች ተገምታ የነበረች አንዲት ሴት፣ ለአንጎል ህክምና ምርምር በለገሰችው የአካል ክፍል አማካኝነት ተገድላ እንደነበር ታወቀ።

በ2010 እ.ኤ.አ. የትምህርት ቤት ፀሐፊ የነበረችው የ47 አመቷ ዳያን ስቱዋርት በቤቷ ውስጥ ህይወቷ አልፎ ተገኘ። ባለቤቷ ኢያን ስቱዋርት ለድንገተኛ አደጋ እርዳታ ደውሎ ዳያን በአትክልት ስፍራው ውስጥ በሚጥል በሽታ እንደወደቀች ተናገረ።

ዳያን የመጨረሻው የሚጥል በሽታ ህመም ያጋጠማት ከ18 ዓመታት በፊት ቢሆንም፣ በወቅቱ በዚሁ በሽታ ምክንያት እንደሞተች ተገምቶ ነበር። የዳያን አስክሬን እንዲቃጠል ቢደረግም፣ አንጎሏ ግን ለሳይንሳዊ ምርምር እንዲለገስ ተደርጎ ነበር።

​ዳያን ከሞተች ከአንድ ዓመት በኋላ፣ ኢያን በሐዘንተኞች መርጃ ቡድን ውስጥ ሄለን ቤይሊ የተባለች የ51 አመት ዝነኛ የልጆች መጽሐፍ ደራሲን አገኘ።

ሁለቱ ተቀራርበው በአንድ ላይ መኖር የጀመሩ ሲሆን ቤትም ገዙ። ነገር ግን የሄለን መጨረሻ እንደ መጀመሪያዋ ሚስቱ እንደ ዳያን ሆነ፤ ኢያን አንቆ ገደላት።

​የአስክሬን ምርመራ ውጤቱን ለወጠው

ኢያን የሄለንን አስክሬን በቤቱ የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ውስጥ ደበቀው። አስክሬኑ ከሦስት ወራት በኋላ ተገኘ። ኢያን በሄለን ግድያ በቁጥጥር ስር ሲውል፣ ፖሊስ የቀድሞ ሚስቱን የዳያንን ሞት በድጋሚ መመርመር ጀመረ።

በምርምር ማዕከል ተጠብቆ የቆየው የዳያን አንጎል በባለሙያዎች በጥልቀት ተመረመረ። ባለሙያዎቹም ሞቷ በሚጥል በሽታ ሳይሆን በኦክስጅን እጥረት ምክንያት የመጣ የአንጎል ጉዳት መሆኑን ደረሱበት።

​በ2022 እ.ኤ.አ. የተጠናቀቀው ምርመራ ኢያን ስቱዋርት በዳያንም ግድያ ጥፋተኛ መሆኑን አረጋገጠ። ኢያን ግድያዎቹን የፈጸመው የኢንሹራንስ ክፍያ ገንዘብ ለማግኘት እንደሆነ ይታመናል። በአሁኑ ወቅት የዕድሜ ልክ እስራት እየፈረደበት ይገኛል።

ባለሙያዎች እንደሚናገሩት ከሆነ ከዚህ ክስተት በኋላ የአንጎል ምርመራ አሠራር ሥርዓት ተለውጧል።

ምንጮች: Sky News፣The Guardian፣ እና BBC News
3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.