Logo
FIDEL POST NEWS
ኳታር በኢነርጂ ተቋማት ላይ በደረሰ ጥቃት የ20 ቢሊዮን ዶላር ኪሳራ ገጠማት

​በኳታር የኢነርጂ ተቋማት ላይ በደረሰ ጥቃት ሀገሪቱ በየዓመቱ የ20 ቢሊዮን ዶላር ገቢ እንደምታጣ አስታወቀች።

የኳታር የኢነርጂ ሚኒስትር ሳድ ሸሪዳ አል ካቢ እንደገለጹት፣ ጥቃቱ የፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ (LNG) የወጪ ንግድ አቅምን በ17 በመቶ ቀንሶታል።

​እንደ ሚኒስትሩ ገለጻ፣ የተጎዱትን የጋዝ ማጣሪያ ተቋማት በሙሉ አቅማቸው ወደ ስራ ለመመለስ እና ጉዳቱን ለመጠገን ከሶስት እስከ አምስት ዓመታት ሊፈጅ ይችላል።

ይህ መስተጓጎል በተለይ ከኳታር ጋዝ በሚያስገቡት እንደ ቻይና፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ጣሊያን እና ቤልጂየም ባሉ ሀገራት ላይ ከፍተኛ የኃይል አቅርቦት ተጽዕኖ ይኖረዋል።
3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.