በኢትዮጵያ የሚሰራው ስፖትላይት ኮሙኒኬሽንስ የ2026 የሳብሬን ሽልማት አሸነፈ
የኢትዮጵያው ስፖትላይት ኮሙኒኬሽንስ ኤንድ ማርኬቲንግ፣ በሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ በዓለም ትልቁና ታዋቂው በሆነው የ2026 ሳብሬ አዋርድስ (SABRE Awards) የዓመቱ ምርጥ ተቋም በመሆን ተሸለመ።
ትላንት በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ በተካሄደው ደማቅ ሥነ-ሥርዓት፣ ተቋሙ ለሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በሠራው የፈጠራ ሥራ ነው የዘርፉን ሽልማት ያገኘው።
ይህ ድል ለአንድ የኢትዮጵያ የፈጠራ ድርጅት በፓን-አፍሪካ ደረጃ የመጀመሪያው በመሆኑ ለሀገሪቱ የሚዲያና ማርኬቲንግ ዘርፍ አዲስ ታሪክ ጽፏል።
በውድድሩ ላይ ከ500 በላይ ዕጩዎች የቀረቡ ሲሆን፣ ስፖትላይት በስትራቴጂክ ጥበቡና በዲጂታል ፈጠራው ቀዳሚ ሆኖ ተመርጧል።
የድርጅቱ የስትራቴጂ መሪ አማኑኤል ብዙአየሁ እንደገለጹት፣ ሽልማቱ የኢትዮጵያ ድርጅቶች በዓለም አቀፍ መድረክ መሪ መሆን እንደሚችሉ ማረጋገጫ ነው ብለዋል።
ስፖትላይት ከመደበኛ የማስታወቂያ ሥራ ባለፈ፣ ለታላላቅ ተቋማትና መንግሥታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች የዕድገት አጋር በመሆን ተጽዕኖ ፈጣሪ ሥራዎችን ማቅረቡን እንደሚቀጥልም አክለዋል።

3 months ago