"የኢራን ቁልፍ ባለሥልጣናት ግድያ፦ መዋቅራችንን አያፈርሰውም’ - የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራቅቺ"
የኔታ ሚዲያ
እስራኤል ከፍተኛ የኢራን ባለሥልጣን የሆኑትን አሊ ላሪጃኒን መግደሏ ቢረጋገጥም ድርጊቱ በሀገሪቱ ከፍተኛ አመራር ላይ ፅገዳይ ድብደባ እንደማያደርስ የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራቅቺ ገለጹ።
ባለፈው ሰኞ ምሽት በተፈጸመ ጥቃት የተገደሉት የ67 ዓመቱ አሊ ላሪጃኒ፣ የኢራን ብሔራዊ ደኅንነት ምክር ቤት ጸሐፊና የሟቹ መሪ አያቶላ አሊ ካሜኒ የቅርብ ረዳት ነበሩ።
ላሪጃኒ ከ19 ቀናት በፊት ጦርነቱ ከተጀመረ አንስቶ እስካሁን የተገደሉ የቴህራን ከፍተኛ አመራር ናቸው።
ሥርዓቱ በአንድ ግለሰብ ላይ የተመሰረተ አይደለም
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አባስ አራቅቺ ከአልጀዚራ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ አሜሪካና እስራኤል የኢራን መንግሥት በአንድ ግለሰብ ላይ እንደማይቆም እስካሁን አለመረዳታቸው አስገርሞኛል ብለዋል።
የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ ጠንካራ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማኅበራዊ ተቋማት መዋቅር አላት። የአንድ ግለሰብ መኖር ወይም አለመኖር ይህን መዋቅር አይነካውም" ሲሉ አራቅቺ አስገንዝበዋል።
ሚኒስትሩ አክለውም የሀገሪቱ የበላይ መሪ አያቶላ አሊ ካሜኒ በየካቲት 21 (Feb 28) በተፈጸመ ጥቃት ቢገደሉም፣ ሥርዓቱ ሳይስተጓጎል ወዲያውኑ ምትክ ተሹሞ ስራውን መቀጠሉን እንደ ምሳሌ ጠቅሰዋል።
የላሪጃኒ ግድያ በተረጋገጠ ማግስት የኢራን የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን የባሲጅ (Basij) ሚሊሻ ኃይል አዛዥ የሆኑት ብርጋዴር ጄኔራል ጎላምሬዛ ሶሌይማኒ "በአሜሪካ-ጽዮናዊ ጠላት" ጥቃት መገደላቸውን በይፋ አረጋግጠዋል። ጄኔራል ሶሌይማኒ ላለፉት ስድስት ዓመታት የኢራንን የውስጥ ደኅንነት ኃይል ሲመሩ የቆዩና በወቅታዊው ጦርነት የአጸፋ ምላሽ ስልት ላይ ቁልፍ ሚና የነበራቸው ሰው ነበሩ።
ሚኒስትር አራቅቺ በክልሉ እየተባባሰ ላለው ግጭት አሜሪካን ተጠያቂ አድርገዋል። "ይህ ጦርነት የእኛ አይደለም፤ እኛም አልጀመርነውም። ለሚከተለው ሰብአዊና ፋይናንሳዊ ኪሳራ ሁሉ አሜሪካ ተጠያቂ መሆን አለባት" ብለዋል።
የፖለቲካ ተንታኞች እንደሚሉት፣ ምንም እንኳን የኢራን የፖለቲካ መዋቅር ጠንካራ ቢሆንም፣ ተከታታይ የከፍተኛ አመራሮች ግድያ በሂደት በሥርዓቱ የጥራትና የውሳኔ አሰጣጥ ብቃት ላይ ተፅዕኖ ማሳደሩ የማይቀር መሆኑን ይገልጻሉ።

3 months ago