Logo
FIDEL POST NEWS
በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በደረቅ ዓሣ ውስጥ ተደብቆ የነበረ ኮኬይን ተያዘ

​በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ 4.48 ኪሎ ግራም ኮኬይን ሊተላለፍ ሲል በቁጥጥር ስር መዋሉን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አስታወቀ።

አደገኛ ዕጹ የተገኘው መነሻውን ናይጄሪያ (ሌጎስ)፣ መዳረሻውን ደግሞ ሕንድ ባደረገ ተጠርጣሪ ሻንጣ ውስጥ ነው።

ዕጹ በደረቀ ዓሣ ውስጥ ተደብቆ ለማለፍ ቢሞከርም፣ በአቪዬሽን ሴኪዩሪቲ ሰራተኞች እና በዘመናዊ የኤክስሬይ መሣሪያ አማካኝነት ሊያዝ ችሏል ተብሏል።

ኮኬይን በድምሩ 172 ፍሬ ወይም 4.48 ኪሎ ግራም የሚመዝን መሆኑ ፖሊስ የገለፀ ሲሆን. ​በአሁኑ ወቅት ተጠርጣሪው እና የተያዘው ዕፅ ለተጨማሪ ምርመራ ለኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ተላልፈው ተሰጥተዋል።
3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.