4.48 ኪሎ ግራም ኮኬይን በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሊተላለፍ ሲል በቁጥጥር ስር ዋለ
4.48 ኪሎ ግራም ኮኬይን በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሊተላለፍ ሲል በቁጥጥር ስር መዋሉን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ገልጿል።
የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ለኢቢሲ በላከው መረጃ እንዳስታወቀው፤ መነሻውን ናይጄሪያ ሌጎስ መዳረሻውን ሕንድ በአደረገ ተጠርጣሪ ሻንጣ ውስጥ ተደብቆ ሊያልፍ የነበረ 4.48 ኪሎ ግራም ኮኬይን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የአቪዬሽን ሴኪዩሪቲ ሰራተኞች ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ባደረጉት ጥብቅ ክትትልና ፍተሻ አማካኝነት በቁጥጥር ስር ውሏል።
172 ፍሬ ብዛት ያለው 4.48 ኪሎ ግራም የሚመዝነው አደገኛ ዕፅ በዓለም አቀፍ መንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል በተገጠመ ዘመናዊ ኤክስሬ መሣሪያ መለየቱን ያመለከተው የአገልግሎት መሥሪያ ቤቱ መረጃ፤ ተጨማሪ ምርመራ እንዲደረግ ተጠርጣሪና ሌሎች መረጃዎች ለኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ መተላላፉቸውን ጠቁሟል።
Via ebc

3 months ago