Logo
YenetaTube
የሠራዊት ጌታ የልዑል እግዚአብሔር አገልጋይ መላዕክት” ቅዱስ ሚካኤል 🙏

የስሙ ትርጓሜ “እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው” ማለት ነው። ድርሳነ ሩፋኤል ላይ ተጽፎ እደምናገኘው 7 ሊቃነ መላዕክት ሲኖሩ አለቃቸው ቅዱስ ሚካኤል ነውከእግዚአብሔር ዙፋን ስር ትዕዛዝ በወጣ ግዜ ኪሩቤል ተቀብለው ለሱራፌል ያስተላልፋሉ፤ ሱራፌልም ለሚካኤልና ለገብርኤል ለሩፋኤልም ያደርሳሉ፡፡ ሚካኤል ለፍጥረቱ በጎም ይሁን ክፉ ትዕዛዙን ይፈጽሙ ዘንድ መላዕክትን ያዛቸዋል፤ ኪሩቤልና ሱራፌል መላዕክቱም ሁሉ አቤቱ የእጅህን ስራ አታጥፋ እያሉ ቀንና ማታ ይለምናሉ። የመላዕክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ከዲያቢሎስ ጋር በተከራከረ ጊዜ እግዚአብሔር ይገስፅህ አለው እንጂ የስድብን ቃል አልተናገረውም ሲባል ሰምተናል፡፡ ሊቀ ነብያት ሙሴ እጅግ ታዛዥና የዋህ ስለነበርና ከነዓንን ለማየት ወደ ናባው ተራራ ሲወጣ 2 መላዕክት በአረጋውያን ተመስለው መቃብር ሲቆፍሩ ቢያይ ላግዛቹ ብሎ መቆፈሪያውን ተቀበላቸው፡፡

በመጨረሻ “ሰውየው በአንተ ልክ ነውና እስቲ ገብተህ ለካልን” አሉት፡፡ እሱም በየዋህነቱ ጉድጓዱ ውስጥ ገብቶ እንደተኛ እንደ እንቅልፍ አሸልቦት በዚያው ዐረፈ፤ መላዕክቱም ቀበሩት። እስራኤላዊያን ሙሴን እጅግ ስለሚወዱት የሙሴን መቃብር እንደ ጣዖት እንዳያመልኩት እግዚአብሔር የሙሴን መቃብር ሰወረው፤ ነገር ግን ጠላት ዲያቢሎስ ሊያሳያቸው በመነሳቱ ቅዱስ ሚካኤል ተቃወመው፡፡ በመጨረሻም ቅዱስ ሚካኤል ዲያቢሎስን እግዚአብሔር ይገስጽህ ብሎ ከእርሱም ሰወረበት። በሐዋርያው ይሁዳ መልዕክት ቁጥር 8 የሚገኘው ቃል የቅዱስ ሚካኤልን ትዕግስት ያሳያል፡፡ ዳግመኛም አይሁድ ጌታን ሲሰቅሉት መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል በቁጣ ሰይፉን አወጣ፤ ቅዱስ ሚካኤል ግን በአይሁድ ስራ አዝኖ፣ ፈጣሪን ፍጡራን ሲሰቀሉት የትዕግስቱንና የፍቅሩን ብዛት እያየ በአርምሞና በትዕግስት አያቸው ይላል ድርሳኑ።

መላዕክቱ በክንፋቸው የእግዚአብሔር ስም ስለተፃፈበት ህዝቡን ይጠብቃሉ፤ የመላዕክቱን ስም የመጨረሻውን ፊደል ስናይ ኤል ብሎ ይጨርሳል፡፡ ሚካ-ኤል ገብር-ኤል ኡራ-ኤል፡፡ ይህም “ስሜ በሱ ላይ ነውና” እንደሚል የእግዚአብሔር የምህረት ስም ስለሆነና በክንፎቻቸው ስለተፃፉ መላዕክቱ ይጠብቁናል። “በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለአንተ ያዛቸዋል፤ እግርህም በድንጋይ እንዳይሰናከል በእጆቻቸው ያነሱሃል” ተብሎም በመዝሙር 90÷11 ተጽፋልና አህዛብን ጭምር ያለጊዜያቸው እንዳይሞቱ መላዕክት ይጠብቋቸዋል!!! ቅዱስ ሚካኤል ሰኔ 12 ቀን ዲያቢሎስን ጥሎ በምትኩ ሊቀ መላዕክት ሆኖ የተሾመበትና አፎምያንም የረዳበት ቀን ስለሆነ በታላቅ ሥርዓት ይከበራል። ህዳር 12 ሕዝበ እስራኤልን በክንፎቹ ጥላ ከበረሃው ፀሐይ ከልሎ ከግብጽ ምድር እየመራና እየጠበቀ ከንዓን ያገባቸው እለት ነው።

በትንቢተ ዳንኤል 10÷13 እና 10÷21 ደግሞ የስሙ ትርጉም እግዚአብሔር ዳኛዬ ነው የተባለው ነብዩ ቅዱስ ዳንኤልም ስለ ቅዱስ ሚካኤል እንዲህ ሲናገር ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ፣ በተዘጋ ጉድጓድ ሲያጽናናው ደግሞ “ከሚካኤል በቀር የሚያጽናናኝ የለም” አለ፡፡ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በመዝሙር 33÷7 “የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል ያድናቸውማል” ይለናል፡፡ በዓለም ፍፃሜም ስለህዝቡ የሚቆመው ሚካኤል ይነሳል። በማለትረ በምዕራፍ 12÷1 ጽፎልናል፡፡ በራዕይ 8÷3 “የቅዱሳኑ ፀሎት ከዕጣኑ ጢስ ጋር ከመልአኩ እጅ ወደ እግዚአብሔር ፊት ወጣ” ተብሎ እንደተጻፈውም መላዕክት የቅዱሳኑን ጸሎት ወደ እግዚአብሔር ያሳርጋሉ፡፡

ገዳማውያንም የእግዚአብሔርን ቸርነት የመላእክቱን አማላጅነት አምነው ዘወትር በጸሎት ይተጋሉ። ገዳማቸውን እየረዳን በዓታቸውን እያጠናን የበረከታቸው ተካፋይ እንሁን፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.