ከመኝታ ሰዓት ሦስት ሰዓት ቀድሞ ምግብ መብላት ማቆም ለልብ ጤና ጥሩ ጥቅም አለው_ጥናት
የኖርዝዌስተርን ሜዲሲን ተመራማሪዎች የተካሄደ አዲስ ጥናት፤ ከመኝታ ሰዓት ሦስት ሰዓት ቀድሞ ምግብ ማቆም ለልብ እና ለሜታቦሊዝም ሥርዓት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው አመለከተ።
በጥናቱ መሰረት የምግብ መጠንን ሳይቀንሱ የምግብ ሰዓትን ብቻ በማስተካከል (ከመኝታ በፊት የ3 ሰዓት ልዩነት በመፍጠር) የሌሊት የደም ግፊትን እና የልብ ምትን በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ ተችሏል።
ከመኝታ በፊት ቀድሞ መመገብ የደም ስኳር መጠንን በማሻሻል ለልብ ሕመም እና ለዓይነት 2 ስኳር በሽታ የሚያጋልጡ ሁኔታዎችን እንደሚቀንስ ተረጋግጧል።
ይህ ዘዴ በተለይ ለልብ ሕመም ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች አመጋገባቸውን ሳይቀይሩ ሊተገብሩት የሚችሉት ቀላል እና ተግባራዊ መፍትሔ መሆኑ ተገልጿል።
የጥናት ውጤቱ “Arteriosclerosis, Thrombosis, and Vascular Biology” በተሰኘው የሕክምና መጽሔት ላይ የታተመ ሲሆን፣ የሰውነታችን የተፈጥሮ የባዮሎጂካል ሰዓት ከምግብ ሰዓት ጋር መጣጣሙ ለጤና ወሳኝ መሆኑን አረጋግጧል።
የምግብ ሰዓትን በማስተካከል ብቻ ከልብ ሕመም፣ ከስኳር እና ከጉበት ስብ ራስን መጠበቅ እንደሚቻልም ተመራማሪዎቹ ገልፀዋል።
ምንጭ፦ Northwestern Medicine / Arteriosclerosis, Thrombosis, and Vascular Biology Journal

3 months ago