ፕሬዝዳንት ትራምፕ የኢራንን ዩራኒየም ወደ ሩሲያ ለማዛወር የቀረበላቸውን የፑቲን የሰላም ዕቅድ ውድቅ አደረጉ
የኔታ ሚዲያ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በኢራን የሚገኘውን የበለጸገ ዩራኒየም ወደ ሩሲያ ለማዛወር ያቀረቡትን ሃሳብ ውድቅ ማድረጋቸው ተሰማ።
አክሲዮስ የተሰኘው የአሜሪካ የዜና ምንጭ እንደዘገበው ትራምፕ ሃሳቡን ውድቅ ያደረጉት በዚህ ሳምንት ከሩሲያው መሪ ጋር በስልክ ባደረጉት ውይይት ወቅት ነው።
ፑቲን ይህንን ሃሳብ ያቀረቡት በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን ጦርነት ለማቆም እንደ አንድ የመፍትሄ አካል ሲሆን ይህም ኢራን ያከማቸችውን 60 በመቶ የበለጸገ ዩራኒየም ወደ ሩሲያ በማዛወር ረገድ የቀረበ ዕቅድ ነበር።
ይሁን እንጂ አንድ የአሜሪካ ባለስልጣን እንደገለጹት "ይህ ሃሳብ ሲቀርብ የመጀመሪያው አይደለም አሁንም ተቀባይነት አላገኘም የአሜሪካ አቋም ዩራኒየሙ በአስተማማኝ ሁኔታ መያዙን ማረጋገጥ ነው ብለዋል።
ኢራን ራሷ ይህንን ሃሳብ አሁን ላይ ትቀበለዋለች ወይ የሚለው ግልጽ አይደለም ከጦርነቱ በፊት በነበሩ ንግግሮች ወቅት ኢራን ዩራኒየሙን ወደ ውጭ የመላክ ሃሳብን ውድቅ በማድረግ ይልቁንም በዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ቁጥጥር ስር በራሷ ተቋማት ውስጥ እንዲቀልጥ የማድረግ ሃሳብ አቅርባ እንደነበር ዘገባው ያስታውሳል።
በሌላ በኩል የትራምፕ አስተዳደር በኢራን የሚገኘውን በከፍተኛ ሁኔታ የበለጸገ ዩራኒየም ለመቆጣጠር ወይም በእጅ ለማስገባት ልዩ የጦር ሃይል (Special Operations Forces) ወደ ስፍራው የመላክ ሃሳብ እያጤነ መሆኑን የተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ባለፈው አርብ ከፎክስ ኒውስ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የበለጸገውን ዩራኒየም ከኢራን ለማስወጣት የታቀደ ወታደራዊ ዘመቻ አለ ወይ ተብለው ሲጠየቁ "አሁን ትኩረታችን እሱ ላይ አይደለም ነገር ግን በተወሰነ ጊዜ ላይ ልናደርገው እንችላለን" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

3 months ago