Logo
FIDEL POST NEWS
መሰረት ደፋር ለሴቶች የ35 ደቂቃ የሩጫ ፈተና አቀረበች

​መጋቢት 13 ቀን 2018 ዓ.ም. የሚካሄደውን የሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5 ኪ.ሜ. የሩጫ ውድድር ምክንያት በማድረግ፣ አትሌት መሰረት ደፋር ተሳታፊዎች ውድድሩን ከ35 ደቂቃ በታች እንዲያጠናቅቁ ጥሪ አቀረበች።

በታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አዘጋጅነት 16 ሺህ ሴቶች በሚሳተፉበት በዚህ ውድድር፣ ተሳታፊዎችን ለማብቃት የ4 ሳምንታት የልምምድ መርሃ ግብር በመከናወን ላይ ይገኛል።

​ዘንድሮ ለ22ኛ ጊዜ የሚካሄደው ይህ ውድድር፣ በስምንት የሥራ ዘርፎች ስኬታማ የሆኑ "ተምሳሌት ሴቶችን" ያሳትፋል።

ከእነዚህም መካከል አርቲስት ቤቲ ጂ፣ ቤተልሄም ደሴ እና መቅደስ ሙሉጌታ ይገኙበታል።

የአሸናፊዎቹ የገንዘብ ሽልማት ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች የሚለገስ ሲሆን፣ የውድድሩ መነሻና መድረሻ ቦሌ አትላስ አካባቢ ይሆናል። ተሳታፊዎች ከመጋቢት 2 እስከ 4 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ ቲሸርታቸውን ከአለም ሲኒማ መውሰድ እንደሚችሉ ተገልጿል።
3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.