Logo
SeledaPost
አጫጭር መረጃዎች

🇮🇱 🇱🇧የእስራኤል ጦር በሊባኖስ ሰሜናዊ ትሪፖሊ ከተማ በወሰደው እርምጃ የሃማስ አዛዥ ዋሲም አታላህ አሊን ላይ ኢላማ በማድረግ መግደሉን አስታውቋል።

🇮🇷🇮🇱🇺🇸 በኢራን ቅዳሜ እለት በሚናብ ትምህርት ቤት ላይ በተፈጸመው የእስራኤል የሚሳኤል 175 ሴት ተማሪዎች እና ሰራተኞችን ጨምሮ ቢያንስ 1,230ዜጎቿ በጦርነቱ ተገድለውባታል። በእስራኤል በኩል እስካሁን 11 ሰዎች ሲገደሉ ስድስት የአሜሪካ ወታደሮችም ተገድለዋል።

🇮🇷🇰🇼 🇦🇪🇧🇭🇴🇲በኢራን የሚሳኤል ጥቃት በኩዌት ወታደሮችን ጨምሮ አራት ሰዎች ፣ በኢምሬትስ ሶስት ፣ በባህሬን እና ኦማን አንድ አንድ ሰዎች ተገድለዋል።

🇱🇧 የሊባኖስ የጤና ሚኒስቴር የእስራኤል የቦምብ ጥቃት ከሰኞ ጀምሮ ባስከተለው ጉዳት 102 ሰዎች ሲገደሉ 638 ሰዎች ቆስለዋል ሲል የሊባኖስ ብሄራዊ የዜና አገልግሎት ዘግቧል።

🇦🇪🌍 የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት የአለም ጤና ድርጅት በዱባይ በሚገኘው የአለም አቀፍ የድንገተኛ አደጋ ሎጂስቲክስ ማዕከል የሚያደርገውን ስራ እንዲያቆም አስገድዶታል ሲሉ ዋና ዳይሬክተሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ገልፀዋል።

🇹🇷🇫🇷 የቱርኪዬ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ለፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እንደተናገሩት አንካራ በኢራን ጉዳይ ላይ ወደ ድርድር እንዲመለስ ግፊት እያደረገች ነው ብለዋል።

🇱🇧🇫🇷 የሊባኖስ ፕሬዝዳንት ጆሴፍ አውን የፈረንሳዩ አቻቸው ኢማኑኤል ማክሮን ጣልቃ እንዲገቡ እና እስራኤል በቤይሩት ደቡባዊ ዳርቻ በዳሂህ ላይ የምታደርሰውን የጅምላ ፍንዳታ እንዲያስቆሙ ጠይቀዋል።

Dagu journal

seledadotio
seledadotio
4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.