የ6 ወር ነፍሰ ጡር ባለቤቱን የገደለው ግለሰብ በዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት ተቀጣ።
የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የ6 ወር ነፍሰ ጡር የነበረችውን ባለቤቱን በአሰቃቂ ሁኔታ በስለት በመቆራረጥ የገደለውን ግለሰብ በዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወሰነ።
የከተማዋ ፖሊስ መምሪያ የወንጀልና ትራፊክ አደጋዎች ምርመራ ም/ዳይሬክተር ኢ/ር ሽመልስ ብሩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለጹት፣ ወንጀሉ የተፈጸመው ታህሳስ 8 ቀን 2018 ዓ.ም በቱላ ክፍለ ከተማ ሀቤላ ወንዶ ቀበሌ ልዩ ስሙ ካፋሪ በሚባል አካባቢ ነው።
ተከሳሹ ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ገደማ ከትዳር አጋሩ ጋር በተፈጠረ ዕለታዊ ግጭት ተነሳስቶ ባለቤቱን በስለት በመቆራረጥ ሕይወቷ እንዲያልፍ አድርጓል።
ግለሰቡ ግድያውን ከፈጸመ በኋላም የሟችን አካል በስለት በመቆራረጥ ወደ ገደል መክተቱን ፖሊስ በምርመራ ወቅት ማረጋገጥ ችሏል።
ፖሊስ ባደረገው ከፍተኛ ማጣራት በሰውና በሰነድ ማስረጃዎች የተደገፈ የምርመራ መዝገብ ለከተማዋ ከፍተኛ ዓቃቤ ህግ ያስተላለፈ ሲሆን፣ ዓቃቤ ህግም በ"ከባድ የሰው ግድያ ወንጀል" ክስ መስርቶበታል።
ጉዳዩን ሲመለከት የቆየው የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀረቡትን የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች ከመረመረ በኋላ ተከሳሹ የፈጸመው ድርጊት እጅግ አስነዋሪና ሰብዓዊነት የጎደለው መሆኑን በማመን " ድርጊቱ ሌሎችን ያስጠነቅቃል ተከሳሹንም ያርማል " ሲል የካቲት 25 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት በግለሰቡ ላይ የዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት ውሳኔ አስተላልፏል።
tikvahethiopia

3 months ago