Logo
YenetaTube
ሼክ ኢብራሂም ቱፋ ከኢራን ጎን መሆናቸውን በይፋ ገለፁ
የኔታ ሚዲያ

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼክ ኢብራሂም ቱፋ በኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ ከፍተኛ መሪ ላይ የደረሰውን ህልፈት ተከትሎ በአዲስ አበባ በሚገኘው የኢራን ኤምባሲ በመገኘት የሃዘን መግለጫ ሰጥተዋል።

ሼክ ኢብራሂም ቱፋ በኤምባሲው ተገኝተው የሃዘን መዝገብ ላይ የፈረሙ ሲሆን በወቅቱም ባስተላለፉት መልዕክት
በደረሰው ጥቃት መሪው በሰማዕትነት ማለፋቸው ለመላው የኢራን ህዝብና መንግስት ታላቅ ሃዘን መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ከኢራን ወንድሞቻቸው ጎን እንደሚቆሙ አረጋግጠዋል።

ይህ ህልፈት ለኢራን ብቻ ሳይሆን ለመላው የዓለም ሙስሊሞች ትልቅ ኪሳራ መሆኑን ሼክ ኢብራሂም ቱፋ በመግለጫቸው ጠቁመዋል።

መረጃው የኢራን ኤምባሲ ነው

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.