Logo
FastMereja
በአፍሪካ ግዙፍ ሪፈራል ሆስፒታል በጮቢ በዓታ ለማርያም ገዳም ሊገነባ ነው።
#fastmereja I ​በምሥራቅ ጉራጌ የሚገኘው የመካነ ሕይወት ጮቢ በዓታ ለማርያም አንድነት ገዳም፣ ባለፉት 20 ዓመታት በመንፈሳዊም ሆነ በልማት ዘርፍ አስደናቂ ውጤቶችን አስመዝግቧል።

​ከ3,000 በላይ ሕፃናትን በመደበኛና በመንፈሳዊ ትምህርት አሳድጓል። ግዙፍ ባለ 8 ፎቅ ርዝመት ያለው ቤተ መቅደስ፣ 8 ኪ.ሜ መንገድ እና የ300 ሺህ ሊትር የውሃ ፕሮጀክት ገንብቷል። በ100 ሄክታር እርሻና በዘመናዊ የወተት ልማት አካባቢውን እየጠቀመ ይገኛል።

ገዳሙ አሁን ደግሞ 1,088 አልጋዎች ያሉትና በአፍሪካ ግዙፍ የተባለውን ሪፈራል ሆስፒታል ግንባታ ጀምሯል! ይህ ፕሮጀክት የሀገራችንን የጤና ችግር ከመቅረፍ ባለፈ ለሕክምና ወደ ውጭ የሚወጣውን ወጪ ያስቀራል ተብሏል።

ሆስፒታሉ በውስጡ ኮሌጅ፣ የህክምና ባለሙያዎች ማረፊያ ከሩቅ ቦታ ለሚምጡ የተመላላሽ ታካሚ ፣ አስታማሚዎች ሆቴሎች እና የተለያዩ ከህክምና ጋር የሚገናኙ ህንጻዎችን ጭምር አካቶ የያዘ ነው ተብሏል።

ሆስፒታሉን ገንብቶ ለማጠናቀቀ ከ1.5 እስከ 2 ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልገ የተነገረ ሲሆን በሰባት አመት ገንብቶ ለማጠናቀቀ እቅድ ተይዟል።

ይህንን ታላቅ ፕሮጀክት ለማጠናቀቅ የካቲት 29 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ጀምሮ ከዮድ አቢሲኒያ ሆቴል (ጉርድ ሾላ) የገቢ ማሰባሰቢያ ቀጥታ ስርጭት ፕሮግራም ተዘጋጅቷል።

​የባንክ አካውንቶች፦
​ንግድ ባንክ፦ 1000571767434
​ወጋገን ባንክ፦ 1125179830101
​አሃዱ ባንክ፦ 0000020010901
​Zelle: +1(310)462 0185 (ኪሩቤል ጌታቸው)

ለተጨማሪ መረጃ 0903280707 / 0913569435

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.