Logo
FIDEL POST NEWS
ኢራን የኒውክሌር ጦር መሣሪያ ስለማምረቷ ማስረጃ የለም ሲል ዓለም አቀፉ የኒውክሌር ተቆጣጣሪ ተቋም ገለፀ

​የዓለም አቀፉ የኒውክሌር ኃይል ኤጀንሲ (IAEA) ዋና ዳይሬክተር ራፋኤል ግሮሲ፣ ኢራን የተቀናጀ የኒውክሌር ጦር መሣሪያ መርሃ ግብር እያከናወነች ስለመሆኑ ምንም ዓይነት ማስረጃ እንዳልተገኘ ገለጹ።

ዳይሬክተሩ ለኤንቢሲ ኒውስ እንደተናገሩት፣ ኢራን ዩራኒየምን እስከ 60 በመቶ የማበልጸግ እርምጃ ብትወስድም፣ ይህ ለሲቪል አገልግሎት ከሚያስፈልገው መጠን እጅግ የላቀ ነው።

​ይህ የዩራኒየም ክምችት በንድፈ ሃሳብ ደረጃ ከ10 በላይ የኒውክሌር አረሮች ለመሥራት ቢበቃም፣ በአሁኑ ወቅት ግን ኢራን ኒኩሌር ቦምብ መሥራቷን የሚያሳይ ፍንጭ የለም ብለዋል።

ይሁን እንጂ ግሮሲ ያለ ግልጽ ዓላማ እንዲህ ያለ ከፍተኛ ክምችት መኖሩ ለኤጀንሲው ትልቅ ስጋት መሆኑን አሳስበዋል።

በሌላ በኩል፣ በእስራኤል እና በኢራን መካከል ያለው ውጥረት እየተባባሰ ባለበት በዚህ ወቅት፣ የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሀገራቸው ለስምምነት ዝግጁ ብትሆንም እጅ እንደማትሰጥ አስታውቀዋል።
4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.