ዓለም በኑክሌር አፋፍ ላይ
የዘጠኙ አገራት አስፈሪ የጦር መሣሪያ ክምችት ዝርዝር ይፋ ሆኗል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው የጂኦ-ፖለቲካ ውጥረት እና የአገራት ወታደራዊ ሽኩቻ እየተባባሰ በመጣበት በዚህ ወቅት የኑክሌር ጦር መሣሪያ የታጠቁ አገራት ቁጥር እና የያዙት የጦር መሣሪያ መጠን የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ዋነኛ የሥጋት ምንጭ ሆኖ ቀጥሏል።
እንደ ፈደሬሽን ኦፍ አሜሪካን ሳይንቲስትስ (FAS) እና መሰል የጥናት ተቋማት እ.ኤ.አ የ2026 መጀመሪያን መረጃ መሠረት በማድረግ ይፋ ባደረጉት ሪፖርት መሠረት በአሁኑ ወቅት በዓለም ላይ ዘጠኝ አገራት ብቻ የኑክሌር ጦር መሣሪያ ባለቤት መሆናቸው ተረጋግጧል።
በዚህ ዝርዝር ውስጥ ሩሲያ በ5 ሺህ 449 የኑክሌር አረሮች ቀዳሚነቱን የያዘች ሲሆን፤ አሜሪካ በ5 ሺህ 277 ክምችት በቅርብ ርቀት ትከተላለች።
እነዚህ ሁለት ልዕለ አያላት ብቻ የዓለማችንን 90 በመቶ የኑክሌር ኃይል የተቆጣጠሩ ሲሆን፥ የቆዩ መሣሪያዎቻቸውን በአዳዲስ የመተካት እና የማዘመን ሥራ ላይ በስፋት ተሰማርተው ይገኛሉ።
ቻይና በበኩሏ ክምችቷን ወደ 600 በማሳደግ በሦስተኛ ደረጃ ላይ ስትቀመጥ ተቀምጣለች።
የአውሮፓዎቹ ፈረንሳይ እና ዩናይትድ ኪንግደም በቅደም ተከተል 290 እና 225 የኑክሌር ጦር መሣሪያዎችን የታጠቁ ሲሆን በእስያ ደግሞ ፓኪስታን 180 እንዲሁም ህንድ 170 የሚጠጉ አረሮችን ይዘው ይገኛሉ።
እስራኤል የኑክሌር ባለቤትነቷን በይፋ ባታምንም በዓለም አቀፍ ደረጃ 90 የሚደርሱ መሣሪያዎች እንዳሏት ይታመናል።
ሰሜን ኮሪያ ደግሞ ምንም እንኳ ቁጥሩን በትክክል ለማወቅ አዳጋች ቢሆንም 50 የሚጠጉ የኑክሌር ጦር መሣሪያዎች ሳይኖሯት እንደማይቀር ይገመታል።
seledadotio

8 months ago