Logo
FIDEL POST NEWS
በምስራቅ ሐረርጌ "ሁለተኛ ልጅ አልወለደችልኝም" በሚል ባለቤቱን የገደለው ግለሰብ በ20 ዓመት እስራት ተቀጣ

​ መሐመድ እና ሟች ወጣት ኢብሲቱ በትዳራቸው የመጀመሪያ ዓመት አንዲት ሴት ልጅ ቢያፈሩም፣ ከዚያ በኋላ ባለቤቱ በድጋሚ ለመውለድ አለመቻሏ በትዳራቸው ውስጥ መቃቃር ፈጥሮ ነበር።

​ተከሳሹ ነሐሴ 15 ቀን 2017 ዓ.ም ምሽት ላይ፣ ባለቤቱ በሰላም ተኝታ ባለችበት ወቅት አስቀድሞ ባዘጋጀው ስለታም ቆንጨራ በመጠቀም በተከታታይ በሰነዘረው ጥቃት ሕይወቷ እንዲያልፍ አድርጓል።

ድርጊቱን የፈጸመው በተለያዩ ተባራሪ ወሬዎች በመገፋፋትና በቅናት ስሜት እንደሆነ ለፖሊስ ቢያምንም፣ በሟች ላይ የቀረበው የክህደት ክስ ግን በማስረጃ አልተደገፈም።

​የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የካቲት 6 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት፣ ድርጊቱ እጅግ አሰቃቂና ነውረኛ መሆኑን ገልጾ፣ በሁለት የቅጣት ማቅለያዎች ግለሰቡ በ20 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ፖሊስ ዋና መምሪያ ገልፇል።
4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.