ወላጆቹ ምድርን የሚያርሱ ክርስቲያን ገበሬዎች ነበሩ፡፡
እርሱም ይህን ዓለም ንቆ ትቶ በሀገረ አክሚም በሚገኝ በአንድ ገዳም መነኰሰ፡፡ ለመብልና ለመጠጥ ሳይገዛ በየሁለት ቀን እየጾመ ለበርካታ ጊዜያት የኖረ ሰማዕቱ ቅዱስ ሚና ሁለተኛ፡፡ ከዚያም ወጥቶ ወደ እስሙናይን ሀገር ሒዶ በአንድ ገዳም ውስጥ እያገለገለና እየተጋደለ ከገዳሙ ደጃፍ ሳይወጣ ዐሥራ ሰባት ዓመት ኖረ።
ያልተጠመቁ አረማውያን በግብጽ ሀገር በነገሡ ጊዜ “እግዚአብሔር ከርሱ ጋር ለዘላለሙ ህልው የሆነ፣ ከባሕርዩ የተወለደ ልጅ፣ የሚሠርፅ መንፈስ ቅዱስም የለውም፣” እንደሚሉ ሰማ ስለዚህም ነገር እጅግ አዘነ። ከነበረበት ገዳም አበ ምኔትም ቡራኬ ተቀብሎ ወደ እስሙናይን ከተማ ወጥቶ ሔደ፡፡
ባልተጠመቁት አረማውያን የሠራዊት አለቃ በሆነ በመኰንኑ ፊት ቁሞም “እናንተ ለእግዚአብሔር ከባሕርዩ የተወለደ ልጅ እንደሌለው አድርጋችሁ የምትናገሩ እውነት ነውን? በማለት ጠየቀው፡፡ መኰንኑም አዎን ልጅ አለው ማለትን ከእግዚአብሔር እናርቃለን አለ። ሰማዕቱ ቅዱስ ሚናስም “ይህን ብላችሁ ልታምኑ አይገባም ነበር፣ እርሱ ያለ ዘር ያለ ሩካቤ ሰው የሆነ አምላክ ነው፤” አለው። መኰንኑም ልጅ አለው ማለት በሕጋችን ክህደት ነው አለ፡፡ አባ ሚናስም መኰንን ሆይ እወቅ የከበረ ወንጌል በወልድ ያመነ የዘላለም ሕይወት አለው በእግዚአብሔር ልጅ በወልድ ያላመነ ሕይወትን አያይም የእግዚአብሔር ቁጣ በላዩ ይወርዳል እንጂ ብሏልና አለው።
ስለዚህም መኰንኑ እጅግ ተቆጣ፤ የካቲት 17 ቀንም አንገቱን በሰይፍም እንዲሰይፍ አደረገ፡፡ ሥጋውንም በየቊርጥራጭ ቆራርጠው በባሕር እንዲጥሉት አዘዘ፡፡ ሰማዕቱ ቅዱስ ሚና ሁለተኛን የሚወዱት ምእመናንም ሥጋውን ወስደው በበጎ አገናነዝ ገንዘው ቀበሩት፡፡
ጌታችንም መታሰቢያውንም የሚያደርጉ ከበረከቱ እንደሚሳተፉ ቃል ኪዳን ገባለት። አምላካችን እግዚአብሔር ለቅዱሳኑ በሚሰጠው ቃል ኪዳን የታመኑ ገዳማውያን ዘወትር ስማቸውን እየዘከሩ ይባረካሉ፡፡ ገዳማቸውን ስንደግፍ በዓታቸውን ስናጸና የበረከታቸው ተሳታፊ እሆናለን፡፡
ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

3 months ago