የጆሮ ማዳመጫዎች ለካንሰር የሚያጋልጡ ኬሚካሎች ተገኙባቸው
በቅርቡ የወጣ አዲስ ዓለም አቀፍ ጥናት እንደሚያመለክተው፣ በገበያ ላይ ባሉ በርካታ ታዋቂ የጆሮ ማዳመጫዎች ውስጥ ለጤና እጅግ አደገኛ የሆኑ ኬሚካሎች ተገኝተዋል። ጥናቱ "የማይታይ ስጋት" (Invisible Threat) ሲል የገለጸው ይህ ግኝት፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተጠቃሚዎችን አስደንግጧል።
🔍 ጥናቱ ምን ይላል?
የአውሮፓው "ToxFree LIFE for All" ፕሮጀክት ሳይንቲስቶች በኦስትሪያ፣ ሃንጋሪ፣ ስሎቫኪያ፣ ስሎቬኒያ እና ቼክ ሪፐብሊክ ገበያዎች እንዲሁም በ Shein እና Temu የኦንላየን ላይ መገበያያ ገጾች የሚሸጡ 81 የጆሮ ማዳመጫዎችን መርምረዋል።
የጥናቱ አስደንጋጭ ውጤቶች፦
100% ተገኝቷል፦ በተመረመሩት ሁሉም 81 የጆሮ ማዳመጫዎች ውስጥ ለጤና ጎጂ የሆኑ ኬሚካሎች ተገኝተዋል።
ታዋቂ ብራንዶች፦ እንደ Bose, Samsung, Panasonic እና Sennheiser ያሉ ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያላቸው ምርቶችም ኬሚካሉ ተገኝቶባቸዋል።
BPA እና BPS፦ በተመረመሩት ምርቶች ውስጥ 98% የሚሆኑት Bisphenol A (BPA) የተባለ ኬሚካል ሲገኝባቸው፣ 75% የሚሆኑት ደግሞ BPS የተባለ ኬሚካል ተገኝቶባቸዋል።
⚠️ ከፍተኛ የኬሚካል መጠን የታየባቸው ሞዴሎች፦
በአንዳንድ ምርቶች ውስጥ ያለው የኬሚካል መጠን የአውሮፓ ኬሚካል ኤጀንሲ (ECHA) ከፈቀደው 10 mg/kg ገደብ በላይ እስከ 315 mg/kg ሆኖ ተገኝቷል። በዝርዝር ከተጠቀሱት መካከል፦
Sennheiser Accentum True Wireless
Bose QuietComfort Headphones እና ሌሎችም ይገኙበታል።
🧪 ኬሚካሎቹ በጤና ላይ የሚያደርሱት ጉዳት፦
እነዚህ "ዘላቂ ኬሚካሎች" (Forever Chemicals) ከጆሮ ማዳመጫው ፕላስቲክ በመላቀቅ በቆዳ በኩል ወደ ሰውነታችን ሊገቡ ይችላሉ። ዋና ዋና ጉዳቶቻቸው፦
ካንሰር፦ ለተለያዩ የካንሰር አይነቶች የመጋለጥ እድልን ይጨምራሉ።
የሆርሞን መዛባት፦ የሴት ሆርሞን (Estrogen) ስለሚመስሉ በወንዶች ላይ የሴትነት ባህሪ (Feminization) እንዲታይ ያደርጋሉ።
የልጆች እድገት፦ በሴት ልጆች ላይ ያለ ዕድሜ ለጉርምስና መዳረግ እና በልጆች ላይ የጭንቅላት እድገት ችግር ያመጣሉ።
የጉበት ጉዳት፦ ለከፍተኛ የጉበት ህመም ይዳርጋሉ።
📢 ምን ይደረግ?
ባለሙያዎች እንደሚመክሩት ተጠቃሚዎች የኦንላይን ገበያዎች የሚገዙ ምርቶችን በጥንቃቄ መመርመር አለባቸው። እንዲሁም ምርቶች "BPA-free" መሆናቸውን ማረጋገጥ ተገቢ ነው።
seledadotio

4 months ago